በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት በቅንጅት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ

0
1091

ንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ላይ እየተስተዋሉ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ቅንጅታዊ አሰራርን ዘርግቶ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ፡፡

በሚኒስቴር መ/ቤቱ የአግሮ ፕሮሰሲንግ እና ፋርማሲዩቲካል ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተካ ገ/እየሱስም ቅንጅታዊ አሰራር ተዘርግቶ እተሰራ መሆኑ በማኒፋክቸሪንግ ዘርፍ ላይ የሚታየውን ችግር እንደሚያቀለው ተናግረዋል፡፡

ጨርቃጨርቅና አልባሳትን ለማምረት ከውጪ የሚገባው ግብዓት ላይ የተጣለው ኤክሳይስ ታክስ ተወዳዳሪ አላደረገንም ጨርቃጨርቅና አልባሳት አምራቾች የኤክሳይስ ታክስ ጫና እና የሎጂስቲክስ ችግር በዘርፉ ያለንን ተስፋ እያሳጣን ነው የሚሉት የኤልቴክስ ጭርቃጨርቅና አልባሳት ፋብሪካ ምክትል ስራ አስኪያጅና የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ካሳሁን ጌታቸው ናቸው፡፡

ከውጪ ለምናስመጣቸው ጥሬ እቃዎች የጉምሩክ የተንዛዛ አሰራርና ቢሮክራሲ ክፉኛ እየጎዳን ነው ያሉት ደግሞ የዲኬ ማኑፋክቸሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ሸር ሆልደር ሚስተር ሊካይድ ሲሆኑ ከውጪ የሚገባው ጥሬ እቃ ኬላ ላይ ከደረሰ በኋላ ጉቦ ካልከፈላችሁ አይለቀቅላችሁም ተብለናልም ይላሉ፡፡

እነዚህንና መሰል ሌሎች ችግሮችን ለመፍታት በዘርፉ በሀገሪቷ ውስጥ ያለውን እድል በሰፊው ለመጠቀም እንዲቻልና በዘርፉ የተሰማሩትን ባለሀብቶች ለማበረታት ብሎም ዘርፉን ከፍ ለማድረግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ቅንጅታዊ አሰራርን በመዘርጋት እየሰራ መሆኑን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስታውቋል፡፡

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here