የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዲኤታ አህመዲን መሃመድ (ፒ ኤች ዲ) የትምህርት ስርዓቱን የዲጂታል ኢኮኖሚው የሚፈልገውን የሰው ሃይል ማፍራት በሚያስችል መልኩ መከለስ እና ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ አሳሰቡ።
“ወደ ዕውቀት-መር ኢኮኖሚ” በሚል የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታው ለትምህርት ዘርፉ በሚያደረገው አስተዋጽኦ ላይ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።
የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ያዘጋጀው ውይይቱ የትምህርት፣ የምርምር፣ የቴክኖሎጂ እና የኢንዱስትሪ ትስስር ኮንቬንሽን፤ ቴክኖሎጂን ለትምህርት ለምርምር እና ለአስተዳደር በዩኒቨርሲቲዎች እና በቴክኒክ እና ሙያ ተቋማት ለመጠቀም በሚያስፈልገው የዲጂታል ስትራቴጂ ላይ ያተኮረ ነው።
የዲጂታል ክህሎት የሌላቸው ዜጎች ከዲጂታል ኢኮኖሚው ለመጠቀም ያላቸው እድል የተገደበ ይሆናል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው የዲጂታል ቴክኖሎጂው የፈጠራቸውን መልካም እድሎች በመጠቀም የትምህርት አሰጣጡን እና አስተዳደሩን የተሳለጠ ማድረግ ይጠይቃል ብለዋል።
የትምህርት ተቋማት ከመማር ማሰተማር እና ምርምር ባሻገር ለዲጂታል ኢኮኖሚው ስኬት ያላቸውን ጉልህ ሚና በመረዳት ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በፓናል ውይይቱ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ለትምህርት ዘርፉ ያለው ሚና፣ የ ዲጂታል ክህሎት ፍኖተ ካርታ አተገባበር፣ መጻኢ ቴክኖሎጂዎች በትምህርት ስረዓቱ ላይ ያላቸው ፋይዳ እና በዲጂታል ትምህርት ሴከተሩ የሴቶች እና የግል ዘርፉ ሚና በሚል የመነሻ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት እንደተደረገባቸው ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተገኘው መረጃ ያስረዳል፡፡







