የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች ከመከላከያ ሰራዊት ጎን እንዲቆሙ ጥሪ ቀረበ

0
809

የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች እንደሌሎች የሀገሪቱ ወጣቶች የመከላከያ ሠራዊትን እንዲቀላቀሉ ለቀረበላቸው ጥሪ አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጡ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጥሪ አቀረቡ።

ምክትል ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ “ውድ የኢትዮጵያ መዲና የአዲስ አበባ ወጣቶች እስካሁን ጀግናውን የመከላከያ ሰራዊታቻንን ለመቀላቀል የተመዘገባችሁና ገና ያልተመዘገባችሁ ፍጠኑ ከወንድሞቻችሁና ከእህቶቻችሁ ጋር ተሰለፉ!” ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

“ኢትዮጵያን በብሔር፣ በሐይማኖትና በሌሎች ምክያቶች በመከፋፈል በማያቋርጥ የውስጥ ግጭት ውስጥ በመክተት አላማቸውን ለማሳካት የነበራቸው ሴራ ከሽፎ፤ ኢትዮጵያዊ አንድነት አንሰራራ ኢትዮጵያውያን ያለ አንዳች ልዩነት ስለ ኢትዮጵያዊያን በአንድነት መቆማቸውን ዳግም አስመሰከሩ።

ውድ የጀግኖች አባቶቻችን የሀገር ፍቅር ፣ የጀግንነት እና የአይበገሬነት ወኔ ዳግም በዚህ ትዉልድ ይደምቃል፤ የዛሬውም የዉክልና ጦርነት በድል ይጠናቀቃል!” ሲሉም መልዕክታቸውን አስፍረዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here