በኢሉባቦር ዞን በፍቃደኝነት መከላከያን ለመቀላቀል የወሰኑ ወጣቶች ተሸኙ

0
732

በኢሉባቦር ዞን በፍቃደኝነት መከላከያ ሠራዊቱን ለመቀላቀል ለወሰኑ ወጣቶች ሽኝት እንደተደረገላቸው ተገለፀ።

የመከላከያ ሠራዊቱን ለመቀላቀል ተመዝግበው ሽኝት የተደረገላቸው ወጣቶችም መንግሥት የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስከበር ያደረገውን ጥሪ ተቀብለው መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።

ወጣት መልካሙ ድሪባ “አባቶች በጀግንነት ሉዓላዊነቷን ጠብቀው ለዛሬ ያደረሷትንና ያስረከቡንን ሀገር ሰላም ለማስከበር መንግስት ያደረገውን ጥሪ በመቀበል በፈቃዴ ተነስቻለሁ” ብሏል።

“የሀገርን ጥሪ ተቀብሎ ሀገር በፈለገችው መስክ ለማገልገል መቆም እድለኛነት ነው” ብሏል ወጣቱ ።

ሱልጣን መሐመድ በበኩሉ “አባቶች በአሸናፊነት ያቆዩልንን ሉዓላዊት ሀገራችን በኛ ዘመን ለጠላት አትንበረከክም፤ እኛም የኛን ድርሻ ለመወጣትና ሀገራችንን ከመፍረስ ለመታደግ ተነስተናል” ሲል ገልጿል።

ትላንት በተዘጋጀው የሽኝት ስነ ስርዓቱ ላይ ለወጣቶቹ መልዕክት ያስተላለፉት የዞኑ ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አቶ መኮንን ባይሳ “አባቶች በደምና በአጥንታቸው የገነቧትንናያስረከቧትን ሀገር ዛሬ ደግሞ ሉዓላዊነቷ ሳይነካ በናንተ ውድ ልጆቿ ተከበራ ትቀጥላለች” ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

“እናት ሀገራችሁ ዛሬ በእናንተ ስለምትኮራባችሁ እንኳን ደስ አላችሁ” ሲሉ ለወጣቶቹ አድናቆትን መቸራቸውም ተገልጿል።

በሽኝት ስነ ስርአቱ ላይ የኃይማኖት አባቶችና አባ ገዳዎች ተገኝተው ወጣቶቹን መርቀዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here