ወደ አዲስ አበባ የሚደረጉ በረራዎች በአቅራቢያ በሚገኙ አውሮፕላን ማረፊያዎች እንዲያርፉ እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ

0
708

በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አካባቢ በተፈጠረው መጥፎ የአየር ጸባይ ምክንያት ወደ አዲስ አበባ የሚደረጉ በረራዎች አቅራቢያ በሚገኙ አውሮፕላን ማረፊያዎች እንዲያርፉ እየተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታውቋል፡፡

አየር መንገዱ ጉዳዩን አስመልከቶ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ላይ ባስተላለፈው መልዕክት፤ በተፈጠረው መጥፎ የአየር ጸባይ ምክንያት ወደ አዲስ አበባ የሚደረጉ በረራዎች አቅራቢያ በሚገኙ አውሮፕላን ማረፊያዎች እንዲያርፉ እየተደረገ መሆኑን አስታውቋል።

የተፈጠረው አየር ጸባይ ችግር ሲስተካከል ለደንበኞቹ እንደሚያሳውቅም አየር መንገዱ የገለጸ ሲሆን ከአየር መንገዱ አቅም በላይ ለተፈጠረው ችግርም ደንበኞችን ይቅርታ ጠይቋል፡፡

በተያያዘ ዜና ማንኛውም የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን የተቀመጠውን መመሪያ የሚጥስ የአውሮፕላን አብራሪም ሆነ ኦፕሬተር ለሚደርሰው አደጋ ሃላፊነት እንደሚወስድ የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ አስጠንቅቋል፡፡

የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ በማህበራዊ ትስስስ ገጹ ላይ ባሰፈረው ጽሁፍ፣ ቀደም ሲል ሰኔ 23 ቀን 2013 ዓ.ም የአየር በረራ መረጃ ማሳወቂያ (NOTAM& AIP SUP) ቁጥር A0166/21 እና AIP SUP A04 ,2021) መተላለፉን አስታውሷል፡፡

በተላለፈው መመሪያ መሠረትም ማንኛውም የአውሮፕላን አብራሪም ሆነ ኦፕሬተር የተቀመጠውን መመሪያ ከጣሰ ለሚደርሰው አደጋ ሃላፊነት የሚወስድ መሆኑን አስታውቋል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here