ባንዴራችን የሚውለበለበው ከሁሉ በላይ ከጀግና ወታደሮቻችን በሚፈልቀው ትንፋሽ ነው፡- ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ

0
1304

ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ በማህበበራዊ የትስስር ገጻቸው ላይ የሻለቃ/ጋዜጠኛ ወይንሐረግ በቀለ “የወታደር ልጅ ነኝ” የተሰኘውን መፅሀፍ በመጥቀስ ስለወታደርነት ሙያና ሊሰጠው ስለሚገባ ክብር መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸውም “ብዙዎቹ የሙያ ዘርፎች ፍላጎትና ተሰጥኦ ይሻሉ። ለውትድርና ግን ቀዳሚው ጉዳይ ጥልቅ የሆነ የሀገር ፍቅር ስሜት ነው። እንደ ሌላው ሙያ ውትድርና እውቀትና ጉልበት ብቻ አይፈልግም፤ ደምና አጥንትን ለመገበር ዝግጁ መሆን ጭምር እንጂ።

ባንዴራችን የሚውለበለበው ከሁሉ በላይ ከጀግና ወታደሮቻችን በሚፈልቀው ትንፋሽ ነው። ታከተኝ ሳይሉ ሀገርን ከማገልገል፣ ሳይሰስቱ ፍቅርን ከመስጠት፣ በመርህ ኖሮ ለመርህ ከመሰዋት የበለጠ አኩሪ ገድል የለም።

ሻለቃ/ጋዜጠኛ ወይንሐረግ በቀለ “የወታደር ልጅ ነኝ” ብላ ስትናገር እጅግ በኩራት ነው። ወታደር መሆን ደግሞ ኩራቱ የትናየት ከፍ እንደሚል አስቡት፡፡ ሳይሰስቱ ሀገር ማፍቀርንና ሳይታክቱ ሕዝብ ማገልገልን ከወታደሮቻችን እንማር!” በማለት አስፍረዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here