በኮሮና ቫይረስ የተዘጉ ትምህርት ቤቶች በድጋሚ እንዲከፈቱ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጥሪ አቀረበ

0
686

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የተዘጉ ትምህርት ቤቶች በድጋሚ እንዲከፈቱ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጥሪ ማቅረቡ ተገለፀ።

ኮቪድ 19 ወረርሽ ሆኖ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን ባለ መረጃ 6 መቶ ሚሊየን የሚደርሱ ተማሪዎች ትምህርታቸዉ አደጋ ላይ ነው ሲል ድርጅቱ አስታውቋል፡፡

የመንግስታቱ ድርጅት የሕፃናት ፈንድ (ዩኒሴፍ) ቃል አቀባይ ጄምስ ኤሌደር በጄኔቫ “መንግስታት የኮሮና ቫይረስ ቀውስ እና የበሽታውን ስርጭት ሊያጋጥማቸው የሚችለዉን ችግር በማሰብ ትምህርት ቤቶችን መዝጋት ከባድ ዉሳኔ መሆኑን እንገነዘባለን፤ ይህ ሊቀጥል አይችልም” ሲሉ ለጋዜጠኞች ገልፀዋል፡፡

“ትምህርት ቤቶች ለመዝጋት የመንግስታት የመጀመሪያ ዉሳኔ እንደነበር ሁሉ በድጋሚ መክፈትም የመጀመሪያ ዉሳኔያቸዉ መሆን ይገባዉ ነበር ሲሉም አሳስበዋል፡፡

ከትምህርት ቤቶች በፊት መጠጥ ቤቶችን እና ሌሎች አገልግሎቶች መጀመሩን አስከፊ ስህተት እንደሆነም ቃል አቀባይዋ ተናግረዋል፡፡

ትምህርት ቤቶችን ለመክፈት ሁሉም መምህራንና ተማሪዎች ክትባት እስኪወስዱ መጠበቅ አይችልም ያሉት ሚኒስትሩ አክለውም ወረርሽኙ ያስከተለው ኢኮኖሚያዊ ችግር ቢኖርም መንግስታት የትምህርት በጀታቸውን ጠብቀዉ እንዲቆዩም ጥሪ አቅርበዋል ሲል ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡

አሜሪካን ጨምሮ በርካታ ሀገራት ትምህርት በኦላን እየሰጡ እንደሚገኙ የሚታወቅ ነው፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here