ቦሌ አለም አቀፍ አዉሮፕላን ማረፊያ ያለዉ የአየር ሁኔታ መሻሻል በማሳየቱ አዉሮፕላኖች ማረፍ መጀመራቸው ተገለፀ

0
1436

ቦሌ አለም አቀፍ አዉሮፕላን ማረፊያ ያለዉ የአየር ሁኔታ መሻሻል በማሳየቱ አዉሮፕላኖች ማረፍ መጀመራቸውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታውቋል።

በአስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ምክንያት ወደ አየር ማረፊያዉ የሚመጡ አዉሮፕላኖች ማረፍ እንደማይችሉ ባለፈዉ ሰኞ መነገሩ የሚታወስ ሲሆን ዛሬ ጠዋት ላይ አዉሮፕላኖቹ ማረፍ መጀመራቸው ተገልጿል፡፡

ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ ወደ ከቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ የሚበሩ አዉሮፕላኖች እያረፉ ሲሆን የአየር ሁኔታዉ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ሙሉ በሙሉ ይስተካከላል የሚል እምነት እንዳለዉ አየር መንገዱ አስታዉቋል ሲል ኢት ኤፍ ኤም ዘግቧል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here