ለሕልውና ዘመቻው ከ25 ሚሊየን ብር በላይ የዓይነት ድጋፍ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለአማራ ክልል ተሰጠ

0
917

ለሕልውና ዘመቻው ከ25 ሚሊየን ብር በላይ የዓይነት ድጋፍ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለአማራ ክልል ተሰጥቷል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሕልውና ዘመቻው የሚያደርገው ድጋፍ በአራት አቅጣጫ የተመራ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ያስታወቁ ሲሆን ለሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ ለአፋር ክልል እና በአማራ ክልል በጎንደር እና በኮምቦልቻ በኩል እንዲደርስ እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

በዓይነት የተደረገው ድጋፍ ከከተማ አስተዳደሩ ባለሃብቶች እና ነዋሪዎች የተሰበሰበ ሲሆን፥ 139 ሰንጋ፣ 1 ሺህ 809 በግና ፍየል፣ በሁለት መኪና የተጫነ ብስኩት፣ 121 ኩንታል ጤፍ እና ምግብ ነክ ቁሳቁስ እንደሆኑ ተነግሯል፡፡

ድጋፉን የተረከቡት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ እና የአማራ ክልል ሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኅላፊ ዶክተር ሙሉነሽ አበበ፥ አዲስ አበባ የኢትዮጵያውያን መዲናነቷን በተግባር ስታረጋግጥ ይህ ድጋፍ የመጀመሪያዋ አይደለም ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ልዑክ ድጋፉ በተጓጓዘባቸው አካባቢዎች ሕዝቡ ላሳየው አብሮነት እና የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ላደረገላቸው አቀባበል አመስግነዋል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here