ገንዘቡና ቁሳቁሶቹ በሌሎች የሃገሪቱ ክፍሎች እንደሚያደርገው ሁሉ ለሚሰጠው ሰብአዊ አገልግሎት ተግባር የሚውል ነው:- አለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ

0
1217
በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ህገ-ወጥ እንደሆኑ ተደርገው ምስላቸው እየተዘወረ የሚገኘው ገንዘብ ቁሳቁሶቹ በሌሎች የሃገሪቱ ክፍሎች እንደሚያደርገው ሁሉ ለሚሰጠው ሰብአዊ አገልግሎት ተግባር የሚውሉ መሆናቸውን አለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ አስታወቀ።
የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታና የህክምና ቁሳቁሶቹም የሚመለከታቸው የፌዴራልና የክልል መንግስት አካላት በቅድሚያ እንዲያውቋቸው ተደርገውና ፈቃድ ተገኝቶባቸው የተጓጓዙ መሆናቸውንም ገልጿል።
ኮሚቴው ምስሉ ላይ የሚታየው ገንዘብ ህገ-ወጥ እንደሆነ የሚገልፅ መልእክት በማህበራዊ ሚዲያዎች እየተዘዋወረ መሆኑን መገንዘቡን ገልፆ፤ ነገር ግን ምስሉ የአለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ አምስት ተሽከርካሪዎች ባካተተው ኮንቮይ ከሁለት ሳምንት በፊት በአፋር ክልል በነበረው ፍተሻ ወቅት የተነሳ መሆኑንም አስረድቷል።
በምስሉ ላይ የሚታዩ ቁሶች በሙሉ የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታና የህክምና ቁሶችንም ያካተተ መሆኑን ጠቅሶ፤ የሚመለከታቸው የፌደራልና የክልል መንግስት አካላት በቅድሚያ እንዲያውቋቸው ተደርገውና ፈቃድ ተገኝቶባቸው የተጓጓዙ እንደሆኑም ገልጿል።
ቁሳቁሶቹና ገንዘቡ በሌሎች የሃገሪቱ ክፍሎች እንደሚያደርገው ሁሉ ለሚሰጠው ሰብአዊ አገልግሎት ተግባር የሚውል ነው ሲልም ኮሚቴው በማህበራዊ ሚዲያዎች እየተናፈሰ ያለውም መረጃ መሰረተ ቢስነት አስረድቷል።
ሁሉም ቁሳቁሶች መቀሌ በሚገኘው የድርጅቱ ቢሮ የደረሱ ሲሆን ጥሬ ገንዘብ የሚያጓጉዝ የባንክ አገልግሎት ባለመኖሩ እንደሆነም ጨምሮ ገልጿል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here