የመንግሥት ሆስፒታሎች በነበራቸው በጥምረት የመሥራት አፈጻጸም 45 ሆስፒታሎች መመረጣችዉ ይታወሳል።
በሆስፒታሎች የሚሰጡ አገልግሎቶች ጥምረትን ለማሻሻል ባለፉት ሦስት ዓመታት የተለያዩ ሥራዎች መሠራታቸውንም ዶ/ር ሊያ ታደሰ ተናግረዋል። በመጀመሪያው ዓመት የተገልጋዮች እርካታ ላይ፣ በኹለተኛው ዓመት በእናቶች እና ሕጻናት ህክምና ትኩረት እንደተደረገም አብራርተዋል።
አሁን በተያዘው እቅድም የሕክምና ተቋማትን ንጽህና በመጠበቅና የተቀላጠፈ አገልግሎት በመስጠት፣ በተለይም በቀዶ ሕክምና አሰጣጥ ላይ ትኩረት በማድረግ፣ የተሠሩ ሥራዎች ላይ ማሻሻያ በማድረግ አጽንዖት ተሰጥቶ እንዲሠራበት ሲሉ ነው የገለጹት።
በዛሬው ዕለት በጤና ሚኒስቴር ዕውቅና በማግኘት ከተመረጡ 45 ሆስፒታሎች ውስጥ በአንደኛ ደረጃ የተቀመጠው ወራቤ ኮምፕረሄንሲቭ ሆስፒታል፣ በኹለተኛ ደረጃ ቢሾፍቱ ጀነራል ሆስፒታል ሲሆን በሦስተኛ ደረጃ ደግሞ የካቲት 12 ሆስፒታል ሁነው መሸለማቸው ተነግሯል።
የጤና ሚኒስትሯ በአጠቃላይ የተጀመረው የተቀናጀ አሠራር፣ ሆስፒታሎችን ምቹ አካባቢ እንዲሆኑ በማድረግ እና በሌሎችም መስኮች በሆስፒታሎች መካከል የሚኖረውን ትስስር በማሳደግ አንጻር ለተገልጋዮች ምቹ የሆነ ሁኔታ ለመፍጠር ያገዛል ብለዋለ።
ለሆስፒታሎችም ከ2 እስከ 3 ሚሊዮን ብር ሽልማት የተሰጠ ሲሆን፣ አጠቃላይ በአገር አቀፍ ደረጃ ከተወዳደሩት ሆስፒታሎች ከአዲስ አበባ የካቲት 12 እና ቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሆስፒታል ብቻ አፈጻጸማቸው አመርቂ ነበር ተብሏል።
ቅጽ 3 ቁጥር 144 ነሐሴ 1 2013


