ከሀገር ውስጥ ታክስ ከዕቅድ በላይ ገቢ መሰብሰቡን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ።የገቢዎች ሚኒስቴር አመራሮች በ2013 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ዛሬ በቢሾፍቱ ከተማ ውይይት እያካሄዱ ነው።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሀገር ውስጥ ገቢ እሰበስባለሁ ብሎ ካቀደው 164 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በላይ በመሰብሰብ ከዕቅድ በላይ አፈፃፀም ማስመዝገቡን ገልጻል።
የክልሎችን የጋራ ገቢ ከማሳደግ አንፃር በተሰሩ ስራዎችም 8 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር የነበረው አጠቃላይ የጋራ ገቢ ምጣኔ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ወደ 22 ነጥብ 08 ቢሊየን ብር ማደጉን አስታውቀዋል።
ይህም ክልሎች የልማት ስራዎቻቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ያስቻለና ከገቢ መስሪያ ቤቱ ጋር ይበልጥ ተቀናጅተው እንዲሰሩ መንገድ የከፈተ መሆኑን አንስተዋል።
በቀጣይ በጀት ዓመት የተስተዋሉ የአሰራር ክፍተቶችን በሚገባ ለይቶ በማረም የተሻለ የገቢ አፈፃፀም እንዲመዘገብ ሁሉም አመራርና ሰራተኛ እንዲሁም ባለድርሻ አካላት በጋራ ሊሰሩ ይገባልም ብለዋል።
ቅጽ 3 ቁጥር 145 ነሐሴ 8 2013


