በየዓመቱ በዐስር የተለያዩ ዘርፎች በየአንዳንዱ ሦስት እጩዎችን እንዲሁም አንድ ልዩ ተሸላሚ የሚለየውና የሚሸልመው የበጎ ሰው ሽልማት ድርጅት ዘጠነኛ ሽልማት እጩዎች ድርጅቱ ኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።
ድርጅቱ ከየካቲት 1 ጀምሮ እጩዎች መቀበል መጀመሩን ያወሱት የድርጅቱ የቦርድ አባል እና ፀሐፊ ቀለመወርቅ ሚደቅሳ፣ ባለፈው ዓመት የቀረቡ እጩዎች ከዘንድሮው ጋር አብሮ መታየቱን ጠቅሰዋል።
ስምንተኛው የበጎ ሰው ሽልማት በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት በልዩ መሰናዶ መከናወኑ ይታወሳል።
በዘጠነኛው የበጎ ሰው ሽልማት እጩዎች ጥቆማ 500 በላይ ጥቆማዎች የቀረቡ ሲሆን በዐስሩ ዘርፎች የመጨረሻ ሦስት እጩዎች ተለይተዋል። በዚህ መሠረት፤
በኪነጥበብ ዘርፍ (ወግና አጫጭር ፅሑፎች)
ጃርሶ ሞትባይኖር ኪሩቤል
በእውቀቱ ስዩም
ታደሰ ሊበን
በማኅበራዊ ዘርፍ
ፕሮፌሰር ጥላሁን ተሾመ
ፕሮፌሰር ጌትነት ታደለ
ዶ/ር አሉላ ፖንክረስት
በመምህርነት ዘርፍ
ፕሮፌሰር ጥሩሰው ተፈራ
ዶክተር ልዑልሰገድ ዓለማየሁ
ፕሮፌሰር በየነ ጴጦሮስ
መንግሥታዊ ኃላፊነትት በብቃት በመወጣት ዘርፍ
ይኩኖአምላክ መዝገቡ
ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ
ኢንጅነር ሀብታሙ ተገኝ
ሚድያና ጋዜጠኝነት ዘርፍ
ደጀኔ ጥላሁን
ዶክተር ንጉሤ ተፈራ
ስለአባት ማናዬ
ቅርስና ባህል ዘርፍ
ሲሳይ ደምሴ
ዶክተር መንግሥቱ ጎበዜ
ቢላሉል ሀበሺ ሙዝየም
በበጎ አድራጎት ዘርፍ
ማሪያ ሙኒር
አማረ አስፋው
እልልታ ውመን
ንግድና ሥራ ፈጠራ ዘርፍ
በላይነህ ክንዴ
ብሩክታዊት ጥጋቡ
ፓን አፍሪክ ሎጂስቲክስ
በሳይንስ ዘርፍ
ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ተፈራ
ዶክተር አየለ ተሾመ
ፖሮፌሰር የወይንሀረግ ፈለቀ
ዳያስፖራ ዘርፍ
ኤልያስ ወንድሙ
ዓለምፀሐም ወዳጆ
ዶክተር እንዳወቅ ይዘንጋው
ከየዘርፉ ከቀረቡ እጩዎች አንድ የዋንጫ ተሸላሚ እንዲሁም በየዓመቱ የድርጅቱ ቦርድ የሚያቀርበው ልዩ ተሸላሚ፤ ነሐሴ 30 በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል በሚካሄደው ዘጠነኛው የበጎ ሰው ሽልማት መርሃ ግብር ይፋ ይደረጋል ተብሏል።



