ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐብይ አሕመድ በቱርክ የሚያደርጉትን ይፋዊ የስራ ጉብኝት ከፕሬዝዳንቱ ጋር በሚያደርጉት ውይይት ጀምረዋል

0
864
ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐብይ አሕመድ በቱርክ የሚያደርጉትን ይፋዊ የስራ ጉብኝት ከፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶጋ ጋር በሚያደርጉት ውይይት መጀመራቸውን የቱርክ ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶጋ በይፋ ጉብኝት በቱርክ ለሚገኙት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ በብሔራዊ ቤተመንግስት ደማቅ የአቀባበል ሥነ ሥርዓት አድርገውላቸዋል።
በሥነ ሥርዓቱ ላይም የቱርክ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙሮች የተዘመሩ ሲሆን በቤተ መንግስቱ የክብር ዘበኞችም ትርዒቶች ቀርበዋል።
በማስከተልም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ የልዑካን ቡድኑን ካስተዋወቁ በኋላ ከፕሬዝዳንቱ ጋር የሁለትዮሽ ስብሰባቸውን ማድረግ መጀመራቸው ታውቋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here