ኢትዮ ቴሌኮም በሚሰጣቸዉ የፓኬጅ አገልግሎቶች ላይ የ20 በመቶ ቅናሽ ማድረጉን አስታውቋል።
ኢትዮ ቴሌኮም በ2014 በጀት ዓመት እቅዱን ይፋ እያደረገ ይገኛል። በበጀት ዓመቱ በርካታ ማሻሻያዎች እና አዳዲስ አገልግሎቶች መፈጠራቸዉን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ ተናግረዋል።
አዲስ ካስተዋወቃቸዉ አገልግሎቶች መካከልም ደንበኞች ከገዙት የጥቅል አገልግሎ ላይ ለሌላ ሰዉ ማጋራት የሚስችል አገልግሎት እንደሚገኝበትም ተገልጿል።



