በእነ ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የክስ መዝገብ ፍርድ ቤት የቀረቡ 21 ተከሳሾች የጠየቁት የዋስትና መብት ውድቅ ተደረገ

0
1021

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ የፀረ ሽብር እና ህገ መንግስታዊ ጉዳዮች ችሎት በእነ ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የክስ መዝገብ ፍርድ ቤት የቀረቡ 21 ተከሳሾች የጠየቁትን የዋስትና መብት ውድቅ መደረጉ ተገለፀ፡፡

በደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል የክስ መዝገብ 58 ግለሰቦች እና አራት ድርጅቶች በሽብር ወንጀል መከሰሳቸው ይታወሳል፡፡

ከእነዚህ መካከል ነሐሴ 11 ቀን 2013 በነበረው ችሎት ከተከሳሾቹ 21ዱ በአካል ቀርበው ክስ የተነበበላቸው ሲሆን የዋስትና መብት እንዲጠበቅላቸውም አመልክተዋል፡፡

ችሎቱ በተከፈተው የክስ መዝገብ ላይ ለዛሬ ይዞት በነበረው ቀጠሮ መሰረት ትዕዛዝን ሰጥቷል፡፡

በተከሾቹ ላይ የተመሰረተባቸው ክስ ዋስትና የሚያስከለክል በመሆኑ ዐቃቤ ሕግ የተለያዩ ዝርዝር ሀሳቦችን በማንሳት መከራከሩም ይታወሳል፡፡

ችሎቱ በሁለቱ ወገኖች ክርክር ላይ ለዛሬ ትዕዛዝ ለመስጠት በያዘው ቀጠሮ መሰረት ተከሳሾች ችሎት መምጣት ሳይጠበቅባቸው በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ሆነው ትዕዛዙን እንዲጠብቁ በማለት ነበር ችሎቱ ለዛሬ የቀጠረው፡፡

ፍርድ ቤቱ የሁለቱንም ወገኖች የዋስትና ጥያቄ ክርክር መርምሮ ዋስትና ጥያቄውን ውድቅ ማድረጉም ታውቋል፡፡

በዚህም መሰረት የፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ በማረሚያ ቤት በኩል ለተከሳሾች እንዲደርሳቸው ሲል ችሎቱ ማዘዙን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

በችሎቱ በአካል ያልተገኙት እነ ደብረጽዮን ገብረሚካኤል፣ ጌታቸው ረዳ፣ ሊያ ካሳ እና ሌሎች ተከሳሾች እንዲሁም የአራቱ ድርጅቶች ተወካዮች የፌዴራል ፖሊስ ባሉበት ይዞ እንዲያቀርብ እና ውጤቱንም ለመጠባበቅ ለጥቅምት 22 ቀን 2014 ተለዋጭ ቀጠሮ መያዙ ይታወሳል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here