ዜናየእለት ዜናበጎንደር ከተማ በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ጥይት ተያዘBy አዲስ ማለዳ - 15/09/20210854 FacebookTwitterWhatsAppTelegram በጎንደር ከተማ በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ከ7 ሺህ በላይ የክላሽና የብሬን ጥይት በቁጥጥር ስር ዋለ።በጎንደር ከተማ ቀበሌ 18 በአንድ አዘዋዋሪ መኖሪያ ቤት በተደረገ ፍተሻ 4 ሺህ 9 መቶ 78 የክላሸና 2 ሺ 7 መቶ 90 የብሬን ጥይት ተይዟል፡፡እንደ ኢብኮ ዘገባ ጥይቶቹን በቁጥጥር ስር ማዋል የተቻለው ብሄራዊ መረጃና ደህንነት ከአማራ ክልል ፖሊስ ጋር በመተባበር ነው።