የድጋፍ ሰጪ አውቶቢሶች ውል ለሦስት ወራት መራዘሙ ተገለጸ

0
816

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የድጋፍ ሰጪ አውቶቢሶች ውል እንዲራዘም ወሰነ።
የድጋፍ ሰጪ አውቶቢሶችን ከመስከረም 4/2014 ጀምሮ ለሦስት ወራት እስከ ታኅሳስ 3/2014 ነው የተራዘመው። በመዲናዋ ድጋፍ ሰጪ አውቶቢሶች ወደሥራ ከገቡ በኋላ በአማካይ 392 አውቶቢሶች በየቀኑ አገልግሎት እንዲሰጡ በመደረጉ የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጡ እንዲሻሻል አስተዋጽኦ አበርቷል።
በኹሉም አውቶቢሶች ላይ ጂፒኤስ (GPS) በመግጠም የክትትልና ቁጥጥር የሚደረግ ሲሆን፣ ይህም በቀን በአማካኝ ለ182 ሺሕ ተጠቃሚዎች አገልግሎት በመስጠት የተሳፋሪ የጊዜ ቆይታን በአማካይ ከ60 ደቂቃ ወደ 12 ደቂቃ ዝቅ በማድረግ አገልግሎት አሰጣጡም እንዲሻሻል ያደርጋል ተብሏል።
ማኅበራትም በውሉ መሠረት የተቀመጡ የአሠራር ሥርዓቶችን ሥራ ላይ በማዋል ከዚህ የተሻለ አገልግሎት እንዲኖር ትኩረት ሰጥተው ሊሠሩ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ከተማ ትራንሥፖርት ቢሮ አሳስቧል።
የከተማ አስተዳደሩ ከጥቅምት 9/2013 ጀምሮ አገር አቋራጭ አውቶቢሶች በኪራይ የትራንሥፖርት አገልግሎት እንዲሰጡ ማደረጉን ከከተማው ፕሬስ ሴክሬታሪ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።


ቅጽ 3 ቁጥር 150 መስከረም 8 2014

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here