ከድር ጁዋር የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ሆነው ተሾሙ
የምስረታ ጉባኤውን እያካሄደ ያለው የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ከድር ጁዋርን የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አድርጎ ሾሟል፡፡
ከድር በአስተዳደሩ በተለያዩ ኃላፊነቶች ማገልገላቸው በእጩነት በቀረቡበት ወቅት ለምክር ቤቱ አባላት በዝርዝር የተገለፀ ሲሆን የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ለመሆን በሙሉ ድምፅ መመረጣቸውም ታውቋል።
ከድር ጁዋር የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሆነው ሲያገለግሉ መቆየታቸው ይታወቃል።
በቀጣይም አዲሱ ከንቲባ የሚያቀርቡትን የካቢኔ አባላት ሹመት ጉባኤው ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
______________________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n




