“ቀጣዮቹ ዓመታት ፈተኛዎች እንደሚያስፈነጥሩን እንጂ አስረው እንደማያስቀሩን የምናሳይበት ጊዜ ይሆናል” ፡-ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ

0
936

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በዓለ ሲመትና የአዲስ የመንግስት ምስረታ ሥነ ሥርዓት በመስቀል አደባባይ ተከናውኗል።

በሥነ ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) “ቀጣዮቹ ዓመታት ፈተኛዎች እንደሚያስፈነጥሩን እንጂ አስረው እንደማያስቀሩን የምናሳይበት ጊዜ ይሆናል” ሲሉ ተናግረዋል።

በቀጣዮቹ ዓመታት ኢትዮጵያ የሚለው ስም ከአይበገሬነት ጋር የተሳሰረ መሆኑን የምናስመሰከርበት እንደሚሆን አልጠራጠርም ያሉት ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)፤ “ኢትዮጵያ ሰንኮፏን የምትነቅልበት፣ ቁስሏን የምታክምበት፣ ህብረ ብሄራዊ አንድነቷን በአለት ላይ የምታፀናበትን ገናናው ስሟን በሰፊው ዓለም ላይ እንዲናኝ የምታደርግበት ዘመን ይሆናል” ብለዋል።

የድህነት አከርካሪ፣ የጥላቻ አንገት፣ የመከፋፈል ወገብ፣ የመፈናቀል ወሽመጥ. መገዳደል ክንድ እና በከንቱ የመወነጃጀል ጉልበት በአገር ልጆች ብርቱ ትብብር ይሰበራል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው።

አክለውም “ፈተናዎች እንደ ወርቅ አንጥረው ያበሯት አገር፤ የአቧራው ብዛትና የቆሻሻው ክምር ወርቅነቷን የማይለውጧት ኢትዮጵያ ትናንት ነበረች፣ ዛሬም አለች ነገ ደግሞ አቧራዋን አራግፋና የቆሻሻዋን ክምር ንዳ ስትነሳ ያኔ ከፊቷ የሚቆም ምንም አይነት ምድራዊ ሃይል አይኖርም” ያሉ ሲሆን ለዚህ ደግሞ ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል አደራ እንዳለበት ተናግረዋል።

በመጨረሻም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) “በቀጣይ ዓመታትም የተጣለብንን አደራ ለመጠበቅና በላቀ ብቃት ለማስፈፀም እንደማናንቀላፋ፣ ያለንን ሁሉ ያለስስት እንደምንሰጥ ለአፍታም እንደማንዘናጋና ቃላችንን እንደምናድስ በመንግስታችን እን በፓርቲያችን ስም በድጋሚ ላረጋግጥ እወዳለሁ” ሲሉም ተናግረዋል።
__________________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mx

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here