10 ምርጥ ኢ-ኮሜርስ ገበያ ተጠቃሚ የዓለም አገራት

0
707

ምንጭ፤ ቢዝነስ ኮም (2021)

በየ ዕለቱ አዳዲስ የኦን ላይን ገበያዎች ብቅ ብቅ ከማለታቸውም አልፈው በሚመሰርቱት ገበያ አዲሰ ምዕራፍ ላይ እየደረሱ ነው። በመሆኑም ከቴክኖሎጀው መዘመን ጋር ተያይዞ የኢ-ኮሜርስ (የኦንላይን) ገበያ በዓለም አቀፍ ደረጃ እያደገ መጥቷል። ቢዝነስ ኮም የተሰኘው ድረ-ገጽ በ2021 ያወጣው መረጃ እንደሚያመላክተው፤ ከላይ የተዘረዘሩት የዓለም አገራት በኢ-ኮሜርስ (በኦን ላይን) ገበያ ተጠቃሚነት አንጻር ግንባር ቀደሞቹ መሆናቸውን ማወቅ ተችሏል።
ከእነዚህም የዓለም አገራት መካከል በኦን ላይን ሽያጭ 35 በመቶ ዕድገት ያሳየችውና በዓመታዊ የሽያጭ ገቢ 672 ቢሊዮን ዶላር ማስመዝገብ የቻለችው ቻይና ስትሆን፤ በዚህም የመጀመሪያውን ደረጃ እንደያዘች ድረ-ገጹ ጠቁሟል።
ከቻይና በመቀጠል በኢ-ኮሜርስ ገበያ የኹለተኛውን ደረጃ የያዘችው ዩናይት ስቴትስ ስትሆን፤ ዓመታዊ የሽያጭ ገቢዋም 340 ቢሊዮን ዶላር ነው ተብሏል።
ከላይ ከተዘረዘሩት 10 የዓለም አገራት መካከልም በኦን ላይን ገበያ በዝቅተኛ ደረጃ የተመዘገበችው በዓመታዊ የኦንላይን ሽያጭ 19 ቢሊዮን ዶላር ያስመዘገበችው ብራዚል መሆኗ የተመላከተ ሲሆን፤ ከዓለም አገራትም 10ኛውን ደረጃ ይዛለች።


ቅጽ 4 ቁጥር 166 ታኅሣሥ 30 2014

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here