የሠሞኑ የመንግሥት ክሥ የማቋረጥ ውሳኔ ዳያስፖራው ላይ ምን ስሜት ፈጠረ?

0
1263

በ2013 ጥቅምት ወር ማብቂያ ገደማ በተቀሰቀሰው እና እስካሁን በዘለቀው ጦርነትሣቢያ ኢትዮጵያ በርካታ ውስጣዊ እና ውጫዊ ጫናዎችን በማስተናገድ ላይ እንደምትገኝ ይገለጻል።

ከውጭ የሚቃጣው ጫና አገር ውስጥ ላለው ጫናመሠረት በመሆን፣ የተለያዩ ታጣቂዎች እንዲፈረጥሙ እና በአገሪቱ የተለያዩ ቦታዎች ሞት እና መፈናቀል እንዲሠፍን አድርጓል። አገሪቱ ላይ ብድርን ከመከልከል ጀምሮ ማዕቀብ እስከመጣል ሊያደርስ የሚችል ከፍ ያለ ጫና አንዣቦባት እንደነበርና አሁንም ድረስ ጫናው ቀንሷል ለማለት እንዳማያስደፍር ነው የሚነገረው።

ይህን ጫና በማርገብ የኢትዮጵያን ችግር ለማቃለል መንግሥትም ይሁን ሕዝብ የራሱን ሚና የሚወጣ ቢሆንም፣ በዚህ ጉዳይ ላይበተለያዩ የውጭ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሚያደርጉት አስተዋጾ ቀላል የሚባል አይደለም።

በዚህም፣ በመላው ዓለም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በተደጋጋሚ ሰልፎችን በማካሄድ ኢትዮጵያ ላይ ጫና የሚያደርጉ አገራት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ በማሳሰብ በአገር ውስጥ ያለው ውጥረትእንዲረግብሲጥሩ እና አገሪቱ ውስጥ ያለውን እውነታ ለዓለም ሲያስረዱ ቆይተዋል።

ከዚህም ባለፈ በውጭ የሚኖሩ የኢትዮጵያ ወገኖች በአገሪቱ ኢኮኖሚ ዘርፍ ላይ ያላቸው አስተዋጾዖ የጎላ መሆኑ አይዘነጋም።አገሪቱ ከውጭ ገበያ ለምታስገባው ምርት እና አገልግሎት በየዓመቱ ከምታወጣው ገንዘብ ውስጥ፣ ከሩብ በላይ የሚሆነው ከዳያስፖራው የሚገኝ መሆኑን የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ይገልጻሉ።

በተጨማሪም፣ የታላቁን ሕዳሴ ግድብ ግንባታ በገንዘብ ከመደገፍ ጀምሮ፣ በግድቡ ምክንያት የሚደርሱ ጫናዎችን ለመቀነስም እስካሁን የዳያስፖራው አባላት ያደረጉት ድጋፍ ከፍተኛ እንደሆነ ይነገራል።

በቅርቡም ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ጉዳት ያስተናገደው የአገር ውስጥ ምጣኔ ሀብት መነቃቃት እንዲፈጠር፣ እንዲሁምየአሜሪካንና የሌሎች ምዕራባውያን አገራት የተሳሳተ አረዳድን ለማስተካከል በሚል በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የቀረበውን ጥሪ ተከትሎ በውጭ የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው ገብተዋል።

ወቅቱምበአገር ውስጥም በውጭም የሚኖሩኢትዮጵያውያንኹሉ በአንድነት ቆመው ያለውን አገራዊ ችግር የሚጋፈጡበት እና ድል የሚያደርጉበት ስለመሆኑ በተደጋጋሚ የሚገለጽ ጉዳይ ነው።

ሆኖም ጥሪውን ተቀብለው በርካታ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ወደ እናት አገራቸው እየመጡ ባለበት፣ መምጣት ያልቻሉትም ለአገራቸው ማድረግ የሚችሉትን ድጋፍ አጠናክረው ለመቀጠል በሚያስቡበት ወቅት፣ታኅሣሥ 29 የገና ምሽት የተሠማው ሠበር ወሬ በርካቶችን ግራ ያጋባ ሆኖ ታይቷል።

በዚህም የእናት አገር ጥሪ ነው በሚል ከዚህ በፊት ለረዥም ጊዜ መጥተው የማያውቁ ዳያስፖራዎች ሳይቀር ወደ አገራቸው መጥተው ደስታቸውን ሳያጣጥሙ፣ በተለይ ማንም ያልጠበቀው በእነ ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የክስ መዝገብ ሥር የነበሩት ስብሀት ነጋ እና ሌሎች አምስት የህወሓት አባላት መፈታት፣ለአገራቸው ሲጨነቁ እና ሲጥሩ ለኖሩ፣ ወደ አገር ቤት ለመጡትም ይሁን ላልመጡት ኢትዮጵያውያን ጥሩ ያልሆነ ስሜት ፈጥሯል ነው የሚባለው።

ሬድዋን ሁሴን ነዋሪነታቸው በለንደን ከተማ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማኅበር የቦርድ አባልና የለንደን ተወካይ ናቸው። በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ እንደገቡ ገልጸው፣መንግሥት ከሠሞኑ በድንገት ዕሥረኞችን መፍታቱ አሳዝኖናል ሲሉ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል። በተፈቱት ሰዎች ምክንያት ብዙ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን አልቀዋል፤ ይህ ባለበት የወገኖቻቸው የሀዘን ልብስ ሳይቀየር መፈታታቸው የሚያሳዝን ነው ሲሉ ገልጸውታል።

የተወሠነው ውሳኔ ትክክል አይደለም ብዬ ነው የማምነው ያሉት ሬድዋን፣ ሆኖም በእናት እና በአገር ማኩረፍ ስለማይቻል ይህ ሆነ ብለን በአገራችን ላይ ፊታችንን አናዞርም የሚል ሐሳብ ሰጥተዋል።

እርግጠኛ ባልሆንም፣ በዚሁ የመንግሥት ውሳኔ የተነሳ በረራቸውን ሠርዘው የተመለሱ፣ እንዲሁም ጉዟቸውን ያጠፉ ዳያስፖራዎች አሉ ይባላል የሚሉት ሬድዋን፣ ዳያስፖራው የተጠራው በግለሰብ አይደለም፤ አገሩ ናት የጠራችው። የሚመጣውም ሕዝቡን አክብሮ ነው በማለት አብራርተዋል።

አያይዘውም፣ የመጣነው ጊዜያችንን፣ ጉልበታችንን እና ገንዘባችንን አጥፍተን ነው። ይህንም ያደረግነው ለመንግሥት ወይም ለግለሰቦች ብለን ሳይሆን፣ በተለይ በገጠሩ ሆኖ ከፍተኛ ጉዳት ለደረሰበት ማኅበረሰብ ብለን ነው ሲሉ ተደምጠዋል።
ዳያስፖራው ይህ ሆነ ብሎ ድጋፉን ማቋረጥ የለበትም። ቢያኮርፍ እና ትብብሩን ቢያቆም የሚጎዳው ምንም ያልተጠቀመው የገጠሩ ሕዝብ እንጂ፣ አራት ኪሎ የሚኖሩ ፖለቲከኞች አይደሉም ባይ ናቸው።

በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ዙሪያ፣ የቨርጅኒያ ነዋሪ ነኝ ያሉት እና አሁን ጥሪውን ተቀብለው ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙት አቤል ጋሼም እንዲሁ ለአዲስ ማለዳ በሰጡት ሐሳብ፣ ዕሥረኞች እንዲፈቱየተወሠነበት የመንግሥት ውሳኔ ምን እየተደረገ ነው የሚያስብልነው። በንጹኃን ላይ የደረሠውን ግፍ እና ሠቆቃ ለሚያውቅ፣ እንዲህ ያሉ የአገርን ሕልውና አደጋ ላይ የጣሉ የጦር ወንጀለኞች ተፈቱ ሲባል ቢደነግጥ እና አንገቱን ቢደፋ የሚገርም አይደለም ብለዋል።

ቢያንስ እንኳን ውሳኔው ለምን እንደተላለፈ ግልጽ ቢደረግ ወይም ደግሞ ከመጀመሪያው ሕዝቡን ያሳተፈ ቢሆን፣ ያን ያህል በውስጥም ሆነ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን ስሜት አይጎዳም ነበር። ሆኖም ግን ለበርካቶች ደም መፍሰስ ቀጥተኛ ተጠያቂ የሆኑ ሰዎች በነጻ ተለቀቁ ስንባል ለምን አናለቅስም ብለዋል።

እነ ስብሀት ነጋን ለመያዝ እኮ ሌላው ቢቀር ወታደሮች ሞተዋል ያሉት አቤል፣ ለተሠውት ወታደሮች ልጆችስ ምን ብለን ነው ታሪኩን የምናስረዳቸው የሚል ሐሳብም አንስተዋል።

ፍትሕሥርዓት አለው። አካሄዱም ግልጽ እና ለሕዝብ ታማኝ መሆን አለበት።ሕዝብም እውነተኛ ሥልጣን እንዳለው ማመን ያስፈልጋል። ውሳኔዎችም ሕዝቡን ያማከሉ ካልሆኑ ዘወትር ከቀውስ ወደ ቀውስ ነው የምንሄደው ሲሉም ነው ያብራሩት።
በዚህም፣ በእንዲህ ዓይነት የማን አለብኝነት ውሳኔ ተበዳይ ሳይካስ የበደለ የሚካስ ከሆነ፣ የሚፈጠረው ቀውስ የከፋ እንደሚሆን አንስተዋል።

ብዙ ዳያስፖራ በዚህ በጣም ቅር ቢሰኝም ቃል ኪዳኑ ከአገሩ ነው፤ ከፖለቲካ ውሳኔ ከፍ ያለ ዕይታ ያለውም ነው ሲሉ ገልጸውታል። ከዚህ ቀደምም በውጭ ምንዛሪ ድጋፍ እና በዲፕሎማሲው ዘርፍ ያበረከተውን ጉልህ አስተዋጾዖአንስተው፣ አሁንም አገሩን ለመገንባት እና እንዲህ ያለው የተዝረከረከ ነገር እንዲወገድ ለማድረግ ጠንክሮ ይሠራል የሚል ዕምነትእንዳላቸው ተናግረዋል።

በህወሓት ዘመን ዳያስፖራው የኢትዮጵያ አንድ አካል መሆኑ ተዘንግቶ ኖሯል ያሉት አቤል፣ ከዚያ በኋላ በተቀየረው ሥርዓት ነገሮች የተስተካከሉ ሲመስሉ ዳያስፖራው ለአገሩ ያለው በጎ ስሜት እና ትብብር በብዙ መልኩ ሲገለጽ ታይቷልም ብለዋል።
አሁንም ዳያስፖራው ለአገሩ ያለው ፍቅር እና ድጋፍ ጥያቄ ውስጥ የሚገባ አይደለም፤ ሆኖም ግን ሕዝባዊ ከበሬታ ከሌለ እና የመንግሥት ተዓማኒነት በየጊዜው እየወረደ የሚሄድ ከሆነ የዚህ ኃይል ድጋፍ በሒደት መታጣቱ አይቀርም ነው ያሉት።

በውጭ የሚኖረው የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ከብዙ ችግሮች ጋር እየተጋፈጠ ኢትዮጵያን አትንኩ በማለት ቁጣዉን የሚገልጽ፣ ትልቅ የሞራል ልዕልና ያለው ኃይል ነው። ስለዚህም ለአገር ግንባታ አንድ አካል አድርጎ በመቁጠር፣ የሚታመን የመንግሥት አሠራር፣ መልካም ፖሊሲ መቅረጽ እና ቀና አፈጻጸም ማሳየት ያስፈልጋል ሲሉ መክረዋል።

የተለያዩ አገሮች ዳያስፖራውን እንደ ትልቅ ኃይል በመቁጠር ለአገረ ግንባታ እንደተጠቀሙበት አመላክተው፣ ለአብነትም በየዓመቱ ለአገራቸው ትልቅ ድጋፍ የሚያደርጉትን በውጭ የሚኖሩ እስራኤላውያንን፣ ሕንዶችን እና ጋናውያንን ዋቢ አድርገዋል።
አቤል ሐሳባቸውን ሲያጠቃልሉም፣ በመንግሥት የተወሠደው ውሳኔ እርሳቸውን ጨምሮ አገራቸውን ለማየት እና በሚችሉት ለማገዝ የመጡ በርካታ ዳያስፖራዎችን ያሳዘነ መሆኑን አንስተው፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ መንፈሳዊ ልዕልናና ሥልጣኔ ያለው፣ አፈር ላይ ተንበርክኮ አምላኩን የሚያመሰግን ትልቅ ሕዝብ በመሆኑ በየጊዜው ቢከዳም ያሸንፋል ነው ያሉት።

ዓለም አቀፉ የኢትዮጵያውያን የተባበረ ዳያስፖራ ጥምረት (International United Ethiopian Diaspora Alliance) በዚሁ ሳምንት መግቢያ ላይ ባወጣው መግለጫ፣በተወሠደው የመንግሥት ዕርምጃ ያደረበትን ቅሬታ አስነብቧል። በዚህም ጥምረቱ በመግለጫው ላይዳያስፖራው ከአገር ውጭ ያለውን የዲፕሎማሲ ትግል ለማሸነፍ ውጤታማ መስዋዕትነት መክፈሉን እና በአገር ውስጥ ለሚካሄደው የሕልውና ጦርነትም ደጀን መሆኑን አትቷል።

በመሆኑም፣ በእንደራሴዎች ምክር ቤት በአሸባሪነት የተፈረጀውን ቡድን ሲመሩ የነበሩ ከሀዲ የጦር ወንጀለኞች መፈታት፣ከፍትሕ አንጻር ሲታይ የተሠጠው ምክንያት እና የተወሠደው ዕርምጃ ትክክል ባለመሆኑ መንግሥት የማስተካከያ ዕርምጃ እንዲወስድ ጥምረቱጠይቋል።
ጥምረቱ በተጨማሪም፣ ስብሀት ነጋ እና ግብረ አበሮቹ ባለፉት 27 ዓመታት በአገሪቱ ላይ ያሳደሩትን ጠባሳ ጠቅሶ፣ አሁንም ተጸጽተው ሕዝቡን ይቅርታ ሳይጠይቁ እና ትጥቅ ሳይፈቱ ከዕሥር መለቀቃቸው የፍትሕሥርዓቱን ተዓማኒነት አደጋ ውስጥ የሚጥል ከመሆኑም በዘለለ፣ ለአገራቸው የተሠው ጀግኖቹን ደም ዋጋ የሚያሳጣ በመሆኑ፣ በአስቸኳይ ተስተካክሎ የሕዝቡን ወሳኝነት፣ ክብር እና ልዕልና ግምት ውስጥ ያስገባ ሕዝባዊ አካሄድ እንዲጠናከር ሲል አሳስቧል።

ዳያስፖራው ሆነ ሕዝቡ የሚፈለገው ለድጋፍ ብቻ ሳይሆን፣ ቅሬታ እና አስተያየቱንም በማዳመጥ ለሚያነሳው ጥያቄ ተገቢ ምለሽ መስጠት እንደሚያስፈልግ ብዙዎች ይናገራሉ።

እስካሁን መንግሥት ከሚወስዳቸው ዕርምጃዎች እና ከሚያሳልፋቸው ውሳኔዎች ጎን በመቆም የሚታወቀው አብዛኛው ዳያስፖራ፣ ከዚህ በኋላስ እንደ ከዚህ ቀድሙ በተጠናከረ መልኩድጋፉ ሊቀጥል ይችላል ወይ የሚል ጥያቄ እየተነሳ ይገኛል።

ተጨማሪ ርዕስ

የዳያስፖራው መምጣት ለሆቴሎች የሚጠበቀውን ገቢ እያስገኘ አለመሆኑ ተገለጸ – ዜና ከምንጩ (addismaleda.com)

ኢትዮጵያ ከዳያስፖራው ምን ትጠብቃለች? – ዜና ከምንጩ (addismaleda.com)

ዳያስፖራው በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ለችግር ለተጋለጡ ዜጎች ከ430 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ – ዜና ከምንጩ (addismaleda.com)


ቅጽ 4 ቁጥር 167 ጥር 7 2014

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here