የእለት ዜና
መዝገብ

Author: ሳሙኤል ታዴ

የተረሱት በደብረ ብርሃን ከተማ የሚገኙ ተፈናቃዮች

በሰሜን ኢትዮጵያ በተከሰተው ጦርነት እንዲሁም በኦሮሚያ፣ ደቡብና ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልሎች በሚነሱ ግጭቶች ሳቢያ ከሞቱት በተጨማሪ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ሀብት ንብረታቸውን ትተው ከቀያቸው ተፈናቅለው በችግር ውስጥ እንደሚኖሩ ይታወቃል። በእንቅርት ላይ እንዲሉ፣ ከዛም ላይ ተፈጥሮአዊ አደጋዎች ታክለው የተፈናቃዩን ቁጥር ጨምሮታል። ኢትዮጵያ ይህን…

ለአማራ ክልል ከሚያስፈልገው የአፈር ማዳበሪያ የገባው 29 በመቶ ብቻ ነው

ለክልሉ አርሶ አደር 769 ሺሕ ኩንታል ብቻ ተሰራጭቷል በዘንድሮው የምርት ዘመን ለአማራ ክልል የሚያስፈልገው የአፈር ማዳበሪያ በዕቅድ የተያዘው 8 ነጥብ 2 ሚሊዮን ኩንታል የነበረ ቢሆንም፣ እስከ አሁን የገባው 29 በመቶ ብቻ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ ለአዲስ ማለዳ ገለጸ። የአማራ ክልል…

በዘጠኝ ወራት 2 ሺሕ 822 የአዕምሯዊ ንብረት መብቶች የምዝገባ አገልግሎት ተሰጥቷል

የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን በዘጠኝ ወራት ውስጥ ባደረገው የአዕምሯዊ ንብረት መብቶች የምዝገባ አገልግሎት፣ በፈጠራ ሥራ ባለቤትነት (Patent)፣ በንግድ ምልክት እና በቅጅ መብት 2 ሺሕ 822 የባለቤትነት መብት መስጠቱን ለአዲስ ማለዳ ገለጸ። ይህም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ880 ወይም…

በሕወሓት ቁጥጥር ሥር በነበሩ ቦታዎች ቤተመጻሕፍት በሙሉ ወድመዋል ተባለ

በሕወሓት ቁጥጥር ሥር በነበሩ የአፋርና አማራ ክልል ቦታዎች ቤተመጻሕፍት በሙሉ ወድመዋል ሲል የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ለአዲስ ማለዳ ገለጸ። ተቋሙ በአፋርና አማራ ክልል ሰባት ዞኖች አካሄድኩት ባለውና ለአዲስ ማለዳ በላከው የጥናት ሰነድ መሠረት፣ በትግራይ ኃይሎች ቁጥጥር ስር በነበሩ ዞኖች፣ ወረዳዎች…

ሺሕዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ የሆኑበት ደቡብ ወሎ ዞን

ዕሮብ ግንቦት 03/2014፤ በዞኑ መቀመጫ ደሴ ከተማ በርካታ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት እያቀኑ ነበር። ሆኖም በአዲስ አበባና ሌሎች ከተሞች እንዳሉ ተማሪዎች እየተሳሳቁና እየቦረቁ ሰብሰብ ብለው የመሄዱን ነገር በሰፊው ሲከውኑት አይታይም። ከዚያ ይልቅ ሁሉም ባይሆን ብዙዎች በተሰላቸ ሞራልና ፈገግታ በራቀው ፊት…

የነዳጅ ዋጋ ጭማሪን ተከትሎ አሽከርካሪዎች በራሳቸው ፈቃድ ከግማሽ በላይ ዋጋ ጨምረዋል

ሰሞኑን የተደረገውን የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ተከትሎ ከአዲስ አበባ ወደ ሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል የሚደረጉ ጉዞዎች ላይ አሽከርካሪዎች በራሳቸው ፈቃድ ከፍተኛ የትራንስፖርት ዋጋ ጭማሪ ማድረጋቸውን አዲስ ማለዳ ተመልክታለች። የተደረገው ጭማሪ በመንግሥት የተደረገ ሳይሆን አሽከርካሪዎች በራሳቸው ያደረጉት ሲሆን፣ ትራንስፖርት ተጠቃሚዎችን በሙሉ ለከፍተኛና አላስፈላጊ…

ከሳዑዲ የሚመለሱ ዜጎችን በቋሚነት ለማቋቋም ምን እየተሠራ ነው?

መሠረት በቃሉ (ስሟ የተቀየረ) ከአረብ አገር ከመጣች ከአንድ ዓመት ተኩል በላይ አልሆናትም። አነስተኛ ቡና ቤት ከፍታ በመሥራት ላይ ትገኛለች። በአረብ አገራት እየተዘዋወረች ስምንት ዓመታትን ብትቆይም ይኖረኛል ብላ ያሰበችውን ያህል ለፍታ ማጠራቀም አልቻለችም። ለአዲስ ማለዳ ስትናገርም፣ ‹‹አረብ አገር ያን ያህል ዓመት…

የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ 20 ሄክታር ደን መጨፍጨፉ ተገለጸ

በሰሜን ጎንደር ዞን የሚገኘው የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ 20 ሄክታር ደን መጨፍጨፉን የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ኃላፊ ለአዲስ ማለዳ አስታወቁ። የፓርኩ ኃላፊ አበባው አዛናው፣ የፓርኩ ዋና ዋና ስጋቶች ከፍተኛ የሆነ ልቅ ግጦሽ፣ ወደ ፓርኩ ተጠግቶ የሚደረግ ሕገ ወጥ የቤት ግንባታ…

የታላቁ የሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ከፍተኛ የበጀት እጥረት እንዳለበት አስታወቀ

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ከፍተኛ የበጀት እጥረት እንዳለበት ለአዲስ ማለዳ ገለጸ። የጽሕፈት ቤቱ የሕዝብ ግንኙነት እና ኮምዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኃይሉ አብርሃም፣ ጽሕፈት ቤቱ በትንሽ የሰው ኃይል በርካታ ሥራዎችን እንደሚሠራ ገልጸው፣ አሁን ላይ ግን ባለው የበጀት እጥረት ብዙ ሥራዎችን…

ፍርድ ቤቶች ለዋስትና የሚይዙት ገንዘብ አብዛኛው ተመላሽ አይሆንም ተባለ

በሕግ ቁጥጥር ውስጥ ሆነው በፖሊስ ምርመራ እየተደረገባቸው ወይም በዐቃቤ ሕግ ክስ ተመስርቶባቸው በገንዘብ ዋስትና የሚለቀቁ ሰዎች፣ ጉዳያቸው ውሳኔ ሳይሰጥበት ተንጠልጥሎ ስለሚቀር የዋስትና ገንዘባቸው እንደማይመለስ ቅሬታቸውን ለአዲስ ማለዳ ገለጹ። በዚህም ፍርድ ቤቶች የዋስትና ገንዘቡን ከሕግ አግባብ ውጭ ለገቢ ምንጭነት እየተጠቀሙበት ነው…

የውሃ አካላት ዳርቻዎችን ርቀት ለመወሰን ረቂቅ አዋጅ እየተዘጋጀ ነው ተባለ

በውሃ አካላትና በየብስ መካከል ያለውን ርቀት ለመወሰን ብሎም በተወሰነው ርቀት መካከል ያለው ድንበር በማስከበር የውሃ አካላትን ደኅንነት ለማስጠበቅ፣ የውሃ አካላትን ዳርቻዎች (በፈር ዞን) ለማልማት እና ለመንከባከብ የሚያስችል ረቂቅ አዋጅ እየተዘጋጀ መሆኑን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ለአዲስ ማለዳ ገለጸ። የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር…

የጣሪያ ላይ የዝናብ ውሃን መጠቀም የሚያስችል ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ ሊውል ነው

የጣራ ላይ የዝናብ ውሃን ሰብስቦ ምድር ውስጥ በማከማቸት ለተለያዩ አገልግሎቶች እንዲውል የሚያስችል ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ ሊውል መሆኑን የኢትዮጵያ የውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ለአዲስ ማለዳ ገለጸ። ቴክኖሎጅው (Roof rain water harvesting) በተለይ በድርቅ የተነሳ የዝናብ እጥረት ባለባቸው እንደ ቦረና፣ አፋር፣ ጉጅና ሶማሌ…

የኢትዮጵያ አርበኞች የድል ቀን ሲታወስ

ከዛሬ 86 ዓመት በፊት 1928 ጣሊያን ኢትዮጵያን በመውረር፣ በዚያው ዓመት ሚያዚያ 27 ማርሻል ባዶሊዮ አረንጓዴ፣ ቢጫ ቀዩን የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ በማስወረድ የጣሊያን ሰንደቅ ዓላማ እንዲሰቀል ማድረጉን ታሪክ ያወሳል። ጣሊያን በ1888 በተካሄደው የአድዋ ጦርነት ጊዜ የደረሰባትን አሰቃቂ ሽንፈት ለመበቀል ለአርባ ዓመታት…

ለአገር አቋራጭ ጉዞዎች ከታሪፍ በላይ በመክፈላቸው ተሳፋሪዎች እየተማረሩ ነው

ከአዲስ አበባ ወደ ክፍለ አገር እንዲሁም ከአንድ ከተማ ወደ ሌላ የሚጓዙ ተሳፋሪዎች ከታሪፍ በላይ በመክፈላቸው እየተማረሩ መሆኑን ለአዲስ ማለዳ ገለጹ። በዚህም ከጊዜ ወደ ጊዜ ትራንስፖርት ሰጭዎች በተሳፋሪዎች ላይ ከሕግ አግባብ ውጪ እያስከፈሉ እንደሆነና ተቆጣጣሪ ባለመኖሩም ኅብረተሰቡን እያማረረ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ቅሬታ…

በዘጠኝ ወራት 66 ሺሕ ቶን የአሳ ምርት ተገኝቷል

በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት 66 ሺሕ ቶን የአሳ ምርት ማግኘት መቻሉን ግብርና ሚኒስቴር ለአዲስ ማለዳ ገለጸ። በግብርና ሚኒስቴር የአሳ ሀብት ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሁሴን አበጋዝ ለአዲስ ማለዳ እንደገለጹት፣ ከሐይቆች 34 ሺሕ ቶን፣ ከግድቦች 20 ሺሕ ቶን እንዲሁም ከወንዞች 11 ሺሕ…

በአማራ ክልል ባልተፈቀደ መሬትና ባልተገነባ ሕንጻ ሕዝቡን የሚያጭበረብሩ አካላት መኖራቸው ተጠቆመ

በአማራ ብሔራዊ ክልል በሚገኙ የተወሰኑ ከተሞች ከሦስተኛ ወገን ነፃ ባልሆነ መሬት ላይ በሚደረግ ሕገወጥ የሪል እስቴት ልማት፣ ባልተፈቀደ መሬትና ባልተገነባ ሕንጻ፣ ሕዝቡን የሚያጭበረብሩ አካላት መኖራቸውን የክልሉ ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ለአዲስ ማለዳ ገለጸ። የቢሮው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ በሰላም ይመኑ፣ በክልሉ…

አበበች ጎበና የሕፃናት ክብካቤና ልማት ማኅበር በምን ሁኔታ ላይ ይገኛል?

አዲስ ማለዳ የፋሲካን በዓል ምክንያት አድርጋ ‹እንኳን አደረሳችሁ! እንዴት ናችሁ?› ስትል ከጎበኘቻቸው መካከል ከተመሠረተ ከአርባ ዓመታት በላይ የሆነው አበበች ጎበና የሕፃናት እንክብካቤና ልማት ማኅበር አንዱ ነው። በደጓ እናት አበበች ጎበና (ነፍስ ኄር) የተመሠረተው ይህ ድርጅት፣ አሁንም የእርሳቸውን ሕልም እውን ለማድረግ…

በማይ-ዓይኒ እና አዲ-ሐሩሽ መጠለያ ከሚገኙ የኤርትራ ስደተኞች አምስት ሺሕዎቹ ሸሽተው ዳባት ገቡ

የቀሩት 18 ሺሕ ስደተኞች “እገታ በሚመስል ሁኔታ ላይ” ናቸው ተብሏል በሕወሓት ቁጥጥር ሥር በሚገኙት የማይ-ዓይኒ እና አዲ-ሐሩሽ መጠለያ ጣቢያዎች ይኖሩ ከነበሩ 23 ሺሕ ገደማ የኤርትራ ስደተኞች መካከል አምስት ሺሕ ገደማ የሚሆኑት የሚደርስባቸውን ጥቃት በመሸሽ አቆራርጠው ወደ አማራ ክልል ዳባት ወረዳ…

የግሪክ ማኅበረሰብ ትምህርት ቤት ከ2014 የትምህርት ዘመን ማብቂያ ጀምሮ መታገዱ ተገለጸ

ከ20 ዓመታት በላይ ሕጋዊ እውቅና ሳይኖረው ለመንግሥት የሚጠበቅበትን ግብር ሳይከፍል ሲያስተምርና ከፍተኛ ገቢ ሲሰበስብ መኖሩ የሚነገርለት የግሪክ ማኅበረሰብ ትምህርት ቤት፣ ከሚቀጥለው የትምህርት ዘመን ጀምሮ ማስተማር እንዲያቋርጥ መታዘዙን ትምህርት ሚኒስቴር ገለጸ። ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ለትምህርት ቤቱ በጻፈው ደብዳቤም፣ ጥር 24/2014 ቀን…

የሴቶች ንፅህና መጠበቂያ ሦስት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከእጥፍ በላይ የዋጋ ጭማሬ አሳየ

የሴቶች ንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ በየጊዜው ከፍተኛ የዋጋ ጭማሬ በማድረግ ላይ ሲሆን፣ በተለይ በቅርቡም ሦስት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከእጥፍ በላይ የዋጋ ጭማሪ አሳይቷል ተብሏል። አዲስ ማለዳ ከተጠቃሚዎች ባገኘችው መረጃ መሠረት፣ ለአብነትም ኮምፎርት የተሰኘው የንጽህና መጠበቂያ ከአንድ ዓመት በፊት በ35 ብር…

ያልተጣጣመው የኤሌክትሪክ ኃይል ፍላጎትና አቅርቦት

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ በመቀጠል ኹለተኛዋ ግዙፍ ኤሌክትሪክ የማመንጨት አቅም ያላት አገር መሆኗ ይነገራል። ይሁን እንጂ የምታመነጨው የኤሌክትሪክ ኃይል አምስት ሺሕ ሜጋ ዋት እንደማይደርስና ይህም የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ጨምሮ በአገሪቱ ያለውን መሠረታዊ የኤሌክትሪክ ኃይል ፍላጎት ለማሟላት በቂ ነው ለማለት እንደማያስደፍር…

የአፋር ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተዘዋዋሪ ችሎት የፍትሕ አገልግሎት መስጠት ጀመረ

የአፋር ብሔራዊ ክልል ቂልበቲ ረሱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተዘዋዋሪ ችሎት የፍትሕ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የክልሉ መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ለአዲስ ማለዳ ገለጸ። መቀመጫው አብዓላ ከተማ የነበረው የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሕወሓት አካባቢውን መቆጣሩን ተከትሎ ወደ ሰመራ ከተማ እንዲዞር መወሰኑን እና በክልሉ…

በአማራ ክልል የተለያዩ ወረዳዎች የኩፍኝ በሽታ ተከሠተ

በአማራ ብሔራዊ ክልል በአራት ወረዳዎች የኩፍኝ በሽታ መከሠቱን የክልሉ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ። ጃቢ ጠህናን፣ ማቻከል፣ ባሶ ሊበን እና ምንጃር ሸንኮራ በተባሉ አራት የክልሉ ወረዳዎች የኩፍኝ በሽታ ወረርሽኝ መከሠቱን የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለአዲስ ማለዳ ገልጿል። የኢንስቲትዩቱ…

ለነዋሪዎቹ ገሀነም ሆኖ የኖረው ወልቃይት ጠገዴ

የኢትዮጵያን የኻምሳ ዓመት ታሪክ የሚያወሱ የጽሑፍ መረጃዎች እንደሚሉት ወታደራዊው መንግሥት ደርግ የአገሪቱን ሥልጣን ተቆጣጠሮ ብዙም ሳይቆይ ታጣቂ ቡድኖች ተፈጥረው ሥርዓቱን ሲታገሉ ቆይተዋል። በተለይ በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈጠሩ የብሔር ፖለቲካ ቡድኖች የኋላ ኋላ የደርግ ሥርዓት ከሥልጣን እንዲወገድ ምክንያት ሆነዋል። በ1968 ደደቢት በረሃ…

የገናሌ ዳዋ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ከስምንት ወር በላይ አገልግሎት መስጠት አቁሟል

የገናሌ ዳዋ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ከስምንት ወር በላይ አገልግሎት መስጠት አቁሟል በደቡብ ምሥራቅ ኢትዮጵያ በዳዋ ወንዝ ላይ የተገነባውና በየካቲት 2012 ተመርቆ ኃይል ማመንጨት የጀመረው የገናሌ ዳዋ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ (Genale Dawa III Hydropower Dam) አገልግሎት መስጠት ካቆመ ከስምንት ወራት በላይ…

በስምንት ወራት ለውጭ ገበያ ከቀረበ የሥጋና ወተት ምርት ከ3.9 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተገኘ

ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 60 በመቶ አድጓል በበጀት ዓመቱ ስምንት ወራት ውስጥ ለውጭ ገበያ ከቀረበ የሥጋና ወተት ምርት ከ3 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘት መቻሉን የኢትዮጵያ ሥጋና ወተት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ለአዲስ ማለዳ ገለጸ። በዚህም ከ16…

የመኪና ባትሪዎችን መልሶ ጥቅም ላይ ለማዋል የሚሠራ ኩባንያ በኢትዮጵያ እየተገነባ ነው

መሠረቱን ኳታር ዶሀ አድርጎ በተለያዩ አገራት በተለያዩ የሥራ መስኮች ላይ ተሠማርቶ እንደሚገኝ የተነገረለት፣ ሱሄይል ግሩፕ (Suhail holding) የተሠኘ ኩባንያ፣ የአገልግሎት ጊዜያቸውን የጨረሱ ‹የሊድ አሲድ› የመኪና ባትሪዎችን መልሶ ጥቅም ላይ ለማዋል የሚችል አምራች ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ ሊከፍት መሆኑን ለአዲስ ማለዳ ገለጸ። የኩባንያው…

“ኤች አር 6600” ምን ተጽዕኖ ይኖረዋል?

በቅርቡ መነጋገሪያ ከሆኑ ጉዳዮች አንዱ የነበረው የአሜሪካ መንግሥት በኢትዮጵያ ላይ ሊያጸድቀው ይችላል የተባለው ኤች አር 6600 ረቂቅ ሕግ ነው። ረቂቁ በርከት ያሉ ዝርዝር ጉዳዮችን በመያዝ በ12 አንቀጾች የተዘጋጀ ነው። ረቂቅ የሕግ ዐዋጁ ‹‹በኢትዮጵያ ሠላምና መረጋጋት፣ እንዲሁም ዴሞክራሲ እንዲሰፍን ለመደገፍ የታሰበ፣…

የኢንዱስትሪ ግብዓቶች አቅራቢ ድርጅት በውጭ ምንዛሪ ዕጥረት ግብዓቶችን ማቅረብ አልቻልኩም አለ

የውጭ ግብዓት አቅርቦት ውሎች እየተሠረዙ ነው የኢንዱስትሪ ግብዓቶች አቅራቢ ድርጅት ለኢንዱስትሪዎች የሚሆኑ ከውጭ የሚገቡ የምርት ግብዓቶችን በውጭ ምንዛሪ ዕጥረት የተነሳ ማቅረብ አልቻልኩም ሲል ለአዲስ ማለዳ ገለጸ። ድርጅቱ ለተለያዩ አምራች ኢንዱስትሪዎች የሚሆኑ ግብዓቶችን ሲያቀርብ እንደቆየ ገልጾ፣ አሁን ላይ ግን በውጭ ምንዛሪ…

በቡራዩ ከ200 በላይ የፍሊደሮ ቀበሌ አባወራዎች ቤታችን በጉቦኛ የቀበሌ ሠራተኞች ሊፈርስ ነው አሉ

በአዲስ አበባ ዙሪያ ቡራዩ ከተማ አስተዳደር ሥር በፍሊደሮ (መልካ ገፈርሳ) ቀበሌ የሚኖሩ ከ200 በላይ አባወራዎች፣ ከ13 ዓመት በላይ የኖርንበት ቤታችን ጉቦ በሚቀበሉ ቀበሌ ሠራተኞች ሊፈርስብን ነው ሲሉ ቅሬታቸውን ለአዲስ ማለዳ ገለጹ። ነዋሪዎቹ አያይዘውም፣ መንግሥት የቆመ ቤት እንዳይፈርስ አዲስም እንዳይሠራ ባለበት…

error: Content is protected !!