አንጋፋዎቹ አዋሽ ባንክ እና ዳሸን ባንክ በታሪካቸው ከፍተኛ የሆነውን ትርፍ አተረፉ

0
523

ሐምሌ 10 ቀን 2016(አዲስ ማለዳ) የ12 ወራት የበጀት አመት መጠናቀቁን ተከትሎ አዋሽ ባንክ 14 ቢሊዮን ብር እንዲሁም ዳሽን ባንክ 6.6 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማግኘታቸውን ገልጸዋል፡፡

በግል የባንክ ዘርፍ አንጋፋ እና ቀዳሚ የሆኑት አዋሽ እና ዳሽን ባንክ በታሪካቸው ከፍተኛውን ትርፍ ማስመዝገባቸውን አዲስ ማለዳ ያገኘችው መረጃ ያመላክታል፡፡

የአዋሽ ባንክ ትርፍ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 4.2 ቢሊዮን ብር ብልጫ አሳይቷል ተብሏል።

ደሸን ባንክ በበኩሉ በ2015 በጀት አመት ከግብር በፊት 5 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱን አዲስ ማለዳ መዘገቧ አይዘነጋም።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here