በተከሰተው የመሬት ናዳ እስካሁን የሟቾች ቁጥር ከ 220 በላይ ደረሰ

0
395

ሐምሌ 16 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) የጎፋ ዞን  አደጋ  ስጋት ስራ አመራር ሃላፊ  አቶ ማርቆስ  መለሰ  በተከሰተዉ  የሟቾች ቁጥር ከ2 መቶ 20  በላይ መድረሱን ተናግረዋል፡፡

በአደጋው ለነብስ አድን ሥራ ቀድመው በስፍራው የተገኙ የቀበሌውን አስተዳዳሪ ጨምሮ መምህራን፣ የጤና ባለሞያዎች እና የግብርና ባለሞያወች የአደጋው ሰለባ ሆነዋል።

አስክሬን የማፈላለጉ ስራዉ ተጠናክሮ እንደቀጠለ የተገለጸ ሲሆን የፌደራሉ መንግስት ድጋፍ እንዲያደርግ ተደጋጋሚ ጥሪ በመቅረብ ላይ ይገኛል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here