የኤርትራ መንግሥት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አሥመራ የሚያደርገው በረራዎች ከመስከረም አጋማሽ በኋላ እንዲቋረጡ ወሰነ

0
394

👉 የኢትዮጵያ አየር መንገድ ውንጀላውን እንደማይቀበል እና የስም ማጥፋት እንደሆነ ገልጿል።

ሐምሌ 17 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) በኤርትራ የትራንስፖርት እና ኮሚዩኒኬሽን ሚኒስቴር የሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ዛሬ በታተመው በመንግሥታዊው “ሓዳስ ኤርትራ” ጋዜጣ ላይ ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ መታገዱን የገልጿል።

ባለሥልጣኑ በጋዜጣው ላይ ባወጣው መግለጫ መሠረት ከመስከረም 20/2017 ዓ.ም. በኋላ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ የሚያደርጋቸው በረራዎችን በሙሉ ማገዱን አስታውቋል።

የሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣኑ አየር መንገዱ እንዲታገድ የተወሰነው “ያልተገባ የንግድ ተግባራት” በመከተሉ ነው ሲል ወቅሷል።

የኤርትራ መንግሥት ከዚህ ውሳኔ ከደረሰባቸው ምክንያቶች መካከል አንዱ በአየር መንገዱ ተጓዦች ላይ “የተደራጀ እና ስልታዊ የሻንጣ ስርቆት” ይፈጸማል የሚለው ይገኝበታል።

ከዚህ በተጨማሪም ተደጋጋሚ የበረራዎች እና የሻንጣዎች መዘግየት እንደሚያጋጥም ጠቅሶ፤ አየር መንገዱ ለተጓዦች ካሳ ሳይሰጥ ቆይቷል ብሏል።

ጉዳዩን በተመለከተ  የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተቋሙ ውንጀላውን እንደማይቀበል እና የስም ማጥፋት እንደሆነ ጠቅሶ “በሰማነው ድንገተኛ ውሳኔ አዝነናል፣ በውሳኔው ዙርያ ማብራርያ ለማግኘት ሙከራዎች እያደረግን ነው ያለ ሲሆን ጉዳዩም በበጎ መልኩ እልባት እንደሚያገኝ ያለውን ዕምነት ገልጿል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሁለት አስርት ዓመታት ቆይታ በኋላ ሀምሌ 11 2011 ዓ.ም ዳግም በረራ ወደ አስመራ መጀመሩ የሚታወስ ነው፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here