
ሐምሌ 22 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት አስፍጻሚ ቦርድ ለኢትዮጵያ የአራት ዓመት የ3.4 ቢሊዮን ዶላር የተራዘመ ብድር አገልግሎት አቅርቦትን አፅድቋል፡፡
የተቋሙ ቦርድ ዛሬ ካጸደቀው ገንዘብ ውስጥ 1 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር አካባቢ የሚሆን ገንዘብ ክፍያ ወዲያውኑ እንዲለቀቅ የሚያስችል መሆኑንም አስታውቋል።
የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ.ኤም.ኤፍ) የስራ አስፍጻሚ ቦርድ ቦርድ ብድሩን ያጸደቀው የኢትዮጵያ መንግስት በገበያ ላይ የተመሰረተ የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርዓት ዛሬ ሰኞ ተግባራዊ ማድረጉን ተከትሎ ነው።


