ዛሬ በሶማሊያ ሊዶ በተሰኘ የባህር ዳርቻ በተፈጸመ የሽብር ጥቃት 32 ሰዎች ተገደሉ

0
238

👉 ይህንን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የተሰማቸውን ሀዘን ገለጸዋል።

ቅዳሜ ሐምሌ 27 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) ጠቅላይ ሚኒስትሩ  ” በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ሀሳባችን እና ጸሎታችን ከተጎጂዎች፣ ከቤተሰቦቻቸው እና ከሶማሊያ ህዝብ ጋር ነው።” ሲሉ በኤክስ ገጻቸው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሹ በሚገኘውና ሊዶ በተሰኘ ተወዳጅ የባህር ዳርቻ መዝናኛ ቦታ አርብ ምሽት በተፈጸመ ጥቃት 32 ሰዎች ሲገደሉ 63 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን የሀገሪቱ ፖሊስ ገልጿል።

ዛሬ ጠዋትም ገሎሌ ሌ ሞቋዲሾ ገሎሌና ባላአጥ መሀል ሌላ በመኪና ላይ የተጠመደ ፍንዳታ ደርሶ በርካቶች መቁሰላቸው ተሰምቷል፡፡

ሮይተርስ እንደዘገበው ስጥቃቱ አሸባሪው አል ሸባብ እንደፈጸመው የሶማሊያ ሚዲያዎች ጠቅሰዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here