የቦንጋ ከተማን ከኮንታና ዳውሮ ዞን የሚያገናኘው አውራ መንገድ በመሬት መንሸራተት ምክንያት ተዘጋ

0
352

ሐሙስ ነሐሴ 02 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) በደቡብና ደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች እየደረሱ ያሉ የመሬት መንሸራተትና የናዳ አደጋዎች የሰው ህይወትን እየቀጠፉ፣ንብረት እያወደሙና ማህበራዊ አገልግሎቶች ላይ መስተጓጎል መፍጠራቸውን ቀጥለዋል፡፡

በትናትናው እለትም በደቡብ ምእራብ ክልል የቦንጋ ከተማን ከኮንታና ዳውሮ ዞኖች የሚያገናኘው አውራ መንገድ በመሬት መንሸራተት አደጋ ምክንያት ስለመዘጋቱ ተሰምቷል፡፡

በካፋ ዞን ጠሎ ወረዳ በጋ ቀበሌ በተለምዶ ዲዶ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በትናንትናው እለት ምሽት ላይ በጣለው ከፍተኛ ዝናብ ምክንያት በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ ነው መንገዱ ሙሉ በሙሉ የተዘጋው።

በዚህ ምክንያት ከጠሎና ከጨታ ወረዳዎች ወደ ቦንጋ የሚደረገው የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ጭምር ተስተጓጉሏል ያለው የጠሎ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የክልሉ መንግስት በአፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥም ጠይቋል።

በደቡብ ኢትዮጵያና በአካባቢው በተደጋጋሚ እየደረሰ ያለው የመሬት መንሸራተት አደጋ አሳሳቢ እየሆነ የመጣ ሲሆን ከሁለት ሳምንት በፊት በጎፋ ዞን በደረሰው የመሬት ናዳ አደጋ ከ260 በላይ ዜጎች ህይወታቸውን ማጣታቸው አይዘነጋም፡፡

የኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ ኢንስቲቲዩትም በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች መሰል አደጋዎች እንደሚከሰቱ በመጠቆም አስፈላጊው ጥንቃቄ እንዲደረግ ማሳሰቡ አይዘነጋም፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here