ዓርብ ነሐሴ 03ቀን2016(አዲስ ማለዳ) በዛሬው ዕለት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ የተለያዩ ሹመቶችን ሰጥተዋል፡፡
ወ/ሪት ሀና ተልህኩ በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ዋና ዳይሬክተር ሆነው ሲሾሙ አቶ ተስፋዬ ይገዙ በመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ እንዲሁም ዶ/ር ብሩክ ታዬ በኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሹመዋል፡፡
አቶ አብዱርሃማን ኢድ ጣሂር የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ፣ ኮማንደር ፍቅሩ አለማየሁ የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ፣ አቶ አብዱልሃኪም ሙሉ በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሹመትን አግኝተዋል፡፡
በተጨማሪም አቶ አብዱርሃማን አብደላ በመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ፣ አቶ ፍቃዱ ተሰማ በሚኒስትር ማዕረግ በዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል፣ ወ/ሮ መስከረም ደበበ በገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ እና ዶ/ር ቢቂላ ሁሪሳ በሚኒስትር ማዕረግ በዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል በመሆን ተሹመዋል



