የዲፕሎማቲክ እና የቆንስላ ሚሲዮኖች ከዚህ በኋላ ወደ ሀገር የሚያስገቡት ተሽከርካሪ በኤሌክትሪክ የሚሰራ ብቻ ነው ተባለ 

0
255

ማክሰኞ ነሐሴ 14 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) በአዲስ አበባ ለሚገኙ የዲፕሎማቲክ እና የቆንስላ ሚሲዮኖች፣ የክልል እና የአለም አቀፍ ድርጅቶች ከዚህ በኋላ ወደ ሀገር የሚያስገቡት ተሽከርካሪ በኤሌክትሪክ የሚሰራ ብቻ ነው ተብሏል።

ይህንን ያለው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው ደብዳቤ ነው።

የዲፕሎማሲ መብት ያላቸው ሁሉ ተሽከርካሪዎችን ከቀረጥ ነፃ እንዲገቡ በተሰጠው አቅጣጫ መሠረት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ብቻ ማስመጣት ይጠበቅባቸዋል ሲል ነው ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ ባሰራጨው ደብዳቤ ያሳወቀው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባሰራጨው በዚህ ደብዳቤ መንግስት ከዚህ ውሳኔ የደረሰው በሀገሪቱ የካርበን ልቀትን ለመግታት እና የነዳጅ ፍጆታን ለመቀነስ ታሳቢ ተደርጎ መሆኑ ተጠቅሷል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here