‹‹በሀገር ደረጃ ይደረጋል የተባለው የደሞዝ ማሻሺያ የመምህራንን ጥቅም ከመቼውም ጊዜ በላይ የሚያስጠብቅ እንዲሆን እንፈልጋለን›› የኢትዮጲያ መምህራን ማህበር

ረቡዕ ነሐሴ 15 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) በሃገር ደረጃ የሚደረገው የደሞዝ ማሻሺያ የመምህራንን ነባራዊ ሁኔታ ከግምት ባስገባ መልኩ እንዲስተካከል እንፈልጋለን ሲል የኢትዮጲያ መምህራን ማህበር አስታውቋል፡፡

የማህበሩ ምክትል ፕሬዚዳንት የሆኑት አቶ ሺመልስ አበበ ከአዲስ ማለዳ ጋር በነበራቸው ቆይታ ምንም እንኳን የደሞዝ ማሻሺያው ገና ተሰርቶ ያላለቀና በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ያልጸደቀ ቢሆንም ማህበሩ የተሸለ የደሞዝ ጭማሪ ለመምህራን ይደረጋል የሚል እምነት እንዳለው ገልጸዋል፡፡

ለዚህም ይረዳ ዘንድ የመምህራን የሙያ ክብደት ምዘና ላይ አስፈላጊውን ጥናት በማከናወን ለሚመለከተው አካል ጥያቄ መቅረቡን ገልጸዋል፡፡
ላለፉት ዓመታት ከደሞዝና ጥቅማጥቅም ጋር በተያያዘ መምህራን ተደጋጋሚ ቅሬታዎችን ሲያሰሙእንደነበር ይታወቃል፡፡

በተለይም በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚያስተምሩ መምህራን የኑሮ ውድነቱ እየተባባሰ በመቀጠሉ በሚያስተምሩበት ተቋም ውስጥ ለተማሪዎቻቸው በተዘጋጁ የማደሪያ ክፍሎች ውስጥ መኖር ግድ እንደሆነባቸው መነገሩ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here