ማክሰኞ ነሐሴ 21 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው ችሎት የፌዴራል ፖሊስ በእነ ዮሀንስ ዳንኤል ላይ የጠየቀውን የ14 ቀን የግዜ ቀጠሮ ፈቅዷል።
ተጠርጣሪዎቹ የዋስትና መብት እንዲፈቀድላቸው በጠበቆቻቸው አማካኝነት የጠየቁ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ የፖሊስን የምርመራ ውጤት ለመጠባበቅ ለጳጉሜ 4 ቀን 2016 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።
ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረቡት ተጠርጣሪዎች ዮሀንስ ዳንኤል በርሄ፣ አማኑኤል መውጫ አብርሃ፣ ናትናኤል ወንድወሰን ሹሜ፣ ኤልያስ ድሪባ በዳኔ፣ ይዲድያ ነጻነት አበበ እና እሌኒ ክንፈ ተክለአብ ናቸው።



