“የደሞዝ ጭማሬው ተስፋ ብቻ ነው የሆነብን”- የመንግስት ሰራተኞች

0
1489

ረዕቡ ነሐሴ 22 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከወራት በፊት የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን በተመለከተ ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ዝቅተኛ የሆነ ወርሃዊ ደመወዝ ለሚከፈላቸው ሠራተኞች እስከ 300 እጥፍ ድረስ የደመወዝ ማሻሻያ ይደረጋል ሲሉ ገልጸው እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ከተናገሩ ጊዜ አንስቶ በተለይም በዝቅተኛ ደሞዝ የሚተዳደሩ የመንግስት ሰራተኞች በተስፋ እየተጠባበቁ መሆናቸውን በተስፋ እየተጠባበቁ እንደሚገኙ በተደጋጋሚ ሲገልጹ ይደመጣል::

አዲስ ማለዳ ያነጋገረቻቸው በተለያዩ የመንግስት መስሪያቤቶች የሚያገለግሉ ሰራተኞችም እስካሁን ምንም አይነት ጭማሬ እንዳልተደረገላቸው እና ማስተካከያው በምንያህልጊዜ ተግባራዊ እንደሚደረግላቸው ጠይቀዋል፡፡

በአንድ የመንግስት ድርጅት በጽዳት ሰራተኛነት የሚሰሩ የሶስት ልጆች እናት እንደገለጹት ካለው የኑሮ ውድነት አንጻር ደሞዛችን እንኳን ቤተሰብ ለማስተዳደር ቤት ኪራይ ለመክፈል እንኳን በቂ አይደለም በዚህ ደግሞ የምንጎዳው ዝቅተኛ ደሞዝ ተከፋዮች ነን ይላሉ፡፡

አክለውም አሁንም ቢሆን በተስፋ ነው እየኖርን ያለነው ይደረጋል የተባለውን ማሻሻያ በተቻለ ፍጥነት ተፈጻሚ ይሁንልን ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ደሞዙ ይጨመራል ሲባል የተወሰነ መረጋጋት ውስጥ ነበርኩኝ እስካሁንም ሊዘገይ የሚገባ ጉዳይ አይደለም ሲሉም የደሞዝ ችማሬው በፍጥነት ተግባራዊ እንዲሆን ጠይቀዋል፡፡

ከአዲስ ማለዳ ጋር ቆይታ ያደረጉ አንድ በሰው ሀይል አስተዳደርነት የሚሰሩ ግለሰብ ደግሞ ጉዳዩ ጊዜ የሚሰጠው ነገር አይደለም በአፋጣኝ ወደ ተግባር ሊቀየር ይገባል ብለዋል፡፡

ፓርላማው ሌሎች አፋጣኝ ጉዳዮችን በቶሎ ሲወሰን አስታውሳለው ያሉት እኚህ አስተያየት ሰጪ ለዚህ አንገብጋቢ የደሞዝ ጭማሪ ጉዳይ ይህን ያህል ጊዜ ሊሰጥ አይገባም ነበር ብለዋል፡፡

በተጨማሪም የመንግስት ሰራተኛው ያለበትን የኢኮኖሚ ችግር ሀገር የሚያውቀው ነገር ነው በአሁን ሰዓት ደግሞ የዋጋ ጭማሪ እና የኑሮ ውድነት ነገሩን እያባባሰው በመሆኑ ወደ ውሳኔ መግባት ያስፈልጋል ሲሉ ጠቁመዋል፡፡

አዲስ ማለዳ በደሞዝ ጭማሪው ዙሪያ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ምን ደረጃ ላይ ደርሷል የሚለውን ለመጠየቅ ወደ ኢትዮጲያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ሃላፊዎች ደጋግማ ብትደውልም መልስ ማግኘት አልቻለችም፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here