ሐሙስ ነሐሴ 30 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ከሶስት ክልሎች አገኘሁት ባለው መረጃ ከወሊድ በኋላ ሴቶችን ወደ ስራ ገበታቸው ያለመመለስ ችግሮች መኖራቸውን አረጋግጫለው ብሏል፡፡
ኢሰመጉ የስራ ቦታ ሁኔታና የሰራተኞችን መብት በተመለከተ ባወጣው መግለጫ በሶስት ዋና ዋና ኢንዱስትሪ ፓርኮች ማለትም በአዲስ አበባ፣ ሐዋሳ እና በደብረብርሃን ጥናት ማድረጉን አመላክቷል፡፡
በዚህም በአማራ ክልል ለሰራተኞች የሚሰጡ ክፍያዎች አነስተኛነት፣ ሴቶች በወሊድ ጊዜ የሚሰጣቸው የወሊድ ፍቃድ አነስተኛ መሆንና አንዳንዴም ፍቃድ ያለመኖር፣ ሰራተኞችን ከወሊድ በኋላ ወደ ስራ ገበታ ያለመመለስ እና መሰል ችግሮች መኖሩን ጠቁሟል፡፡
የሲዲማ ብሔራዊ ክሌሊዊ መንግስት የሥራና ክህልትና ኢንተርፕራይዝች ልማት ቢሮ በአሰሪና ሰራተኛ ዘርፍ በሰላማዊ ኢንዱስትሪ ዲይሬክቶሬት የተገኘ መረጃ በአጠቃሊይ በኢንዱስትሪ ፓርኩ ውስጥ ያሉ አሰራሮች ሕጉን ተከትለው እየተከናወኑ እንዳለ መግለፁን ጉባኤው አስታውቋል፡፡
በአንጻሩ በሐዋሳ የሚገኙ ኢሰመጉ ያነጋገራቸው ሰራተኞች በተወሰኑ ፋብሪካዎች ላይ የሚከናወኑ ህፈወጥ ተግባራት እና በሴት ሰራተኞች ላይ የሚደርሰውን በደል መናገራቸውን አያይዞ ገልጻል፡፡
በአዲስ አበባ በሚገኙ ኢንዱስትሪ ፓርኮችም ተመሳሳይ ችግር እንዳለ ጠቅሷል፡፡
የኢንደስት ሪፓኮችን አጠቃላይ ሁኔታ በተመለከተ ኢሰመጉ ለኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ሴቶች ማህበራዊ ጉዲይ ሚንስቴር እና ለአዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በደብዳቤ የጠየቀ ቢሆንም ምላሽ አላገኘሁም ብሏል፡፡
በመጨረሻም ጉባኤው መንግስት በአገር አቀፍ ደረጃ ዝቅተኛ የደመወዝ መጠንን በማስቀመጥ በኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች ለሚሰሩት ስራ ተመጣጣኝ ክፍያ እንዱያገኙ፣ በቂ የሆነ የኑሮ ደረጃ መኖር የሚያስችል ክፍያ እንዱያገኙእና መሰረታዊ ፍላጎቶችን የሚያሟላ ክፍያ እንዲያገኙ እንዱያደርግ አሳስቧል፡፡



