ጃዋር መሀመድ በኦነግ አመራሮች መፈታት መደሰታቸውን ገለጹ

0
355

ሐሙስ ነሐሴ 30 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ)

ጃዋር መሀመድ በኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ከፍተኛ አመራሮች መፈታት መደሰታቸውን ገለጹ።

አቶ ጀዋር ለ4 ዓመታት ያህል በግፍ ታስረው የቆዩት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) አመራሮች ከእስር መለቀቃቸውን ከእስር እንዲለቀቁ መደረጉን አወድሰዋል።

አቶ ጀዋር ማምሻውን በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት በአመራሮቹ መፈታት እጅጉን ስለመደሰታቸው ገልጸዋል።

መቀመጫውን ከሀገር ውጪ ያደረጉት ፖለቲከኛ ጀዋር መንግስት የቀሩትን የፖለቲካ እስረኞች በመፍታት የትጥቅ ግጭቶችን በሙሉ በውይይትና በድርድር እንዲቆሙ በማድረግ በአመራሮቹ ላይ ያሳየውን በጎ እርምጃ እንዲያሳድግ ሲሉ ጠይቀዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here