ኢትዮቴሌኮም ከነገ ጀምሮ የታሪፍ ማሻሻያውን ተግባራዊ አደርጋለሁ አለ

0
363

ሰኞ መስከረም 20 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) መንግስታዊው የቴሌኮም አቅራቢ ድርጅት ኢትዮቴሌኮም ከነገ መስከረም 21 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ በተወሰኑ ምርትና አገልግሎቶቹ ላይ የዋጋ ማሻሻያ አደርጋለሁ ብሏል።

ተቋሙ የሚደረገው የዋጋ ማሻሻያ አብዛኛውን የህብረተሰብ ክፍል እንደማይነካ የገለፀ ሲሆን ተመጣጣኝ እና የዲጅታል አካታችነትን መርህን በጠበቀ መልኩ ተግባራዊ ይደረጋል ሲል ገልጿል።

ተቋሙ የሚደረገዉ ማሻሻያዉ 22 ፓኬጆችን የማይነካ እንደሆነ ቢገልፅም በምን ያህል ፐርሰንት የሚለዉን እና በየትኞቹ አገልግሎቶቹ ላይ  ተግባራዊ እንደሚደረግ አላሳወቀም።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here