የትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት መስክ የምርጫ መሙያ ጊዜውን አራዘመ

ሐሙስ መስከረም 30 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) በ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በመደበኛ እና በ ‘Remedial’ ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም እና የትምህርት መስክ ምርጫቸውን በየትምህርት ቤታቸው በተወከሉ መምህራን በኩል ሞልተው እንዲያስረክቡ አስታውቆ ነበር፡፡

እስከ መስከረም 30 ድረስ ሞልተው እንዲጨርሱ የተገለጸ ቢሆንም አንዳንድ ትምህርት ቤቶች በሲስተም ችግር ምክንያት የተማሪዎቻችንን የትምህርት መስክ እና የዩኒቨርስቲ ምርጫ መሙላት ተቸግረናል ” ብለዋል፡፡

በመሆኑም የትምህርት ሚኒስቴር የምርጫ መሙያ ጊዜውን እስከ ረቡዕ ጥቅምት 6ቀን2017 ዓ.ም ድረስ ማራዘሙን ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here