ሰኞ ህዳር 23፡2017 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጸጥታ ክፈል ባልደረባ ፍሬዘር በቀለ ህዳር 16 2024 ዐ.ም ከመንገደኛ ወድቆ ያገኙትን 50 ሺህ ያሜሪካን ዶላር ለባለቤቱ ማስረከባቸውን አየርመንገዱ አስታውቋል ።
አየር መንገዱ ባልደረባችን በኢትዮጵያዊ ጨዋነት እና ሲቀጠሩ በገቡት ቃል መሰረት የሚመራበትን መርህ እና ስነ ምግባር እንዲሁም ሙያዊ ታማኝነታቸዉን በብቃት በመወጣት አስመክረዋል ሲል ባወጣው መግለጫ ጠቅሷል ።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ እና ስነ መግባር የተላበሰ የደንበኞች አገልግሎት ለመስጠት ሁሌም አንደሚተጋም ባስተላፈው መልእክት ገልጿል፡፡



