መንግስት ያለበትን የሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ በአግባቡ ባለመወጣቱ የመብት ጥሰቶች እየቀጠሉ ነው- ኢሰመጉ 

0
150

ዕረቡ ታህሳስ 02 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በዓለም አቀፍ ደረጃ በታህሳስ 01 የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ መግለጫ አውጥቷል፡፡

በዚህም መግለጫ መንግስት ያለበትን የሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ በአግባቡ ባለመወጣቱ የሰብዓዊ መብቶች አሁንም እየተጣሱ ይገኛሉ ብሏል፡፡

ኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በመንግስትና በታጠቁ አካላት እንዲሁም ሰላም እንዳይሰፍን በሚሰሩ በተለያዩ አካላት እየተፈጸመ ያለው ዘርፈብዙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መሆኑንም አመላክቷል፡፡

በመሆኑም በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች ላይ ሞት፣ የአካል ጉዳት፣ እገታ እና አፍኖ መሰወር፣መፈናቀል፣ ንብረት ውድመት እና ለሌሎች የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች የተዳረጉ ሲሆን አሁንም በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች እንደቀጠለ ባለው የትጥቅ ግጭት ከፍተኛ የሆነ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች እየተፈጸመ መሆኑን ገልጿል።

በአንጻሩ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ክፍሎች በሚንቀሳቀሱ የተወሰኑ የታጠቁ አካላት እና በኦሮሚያ ክልል መንግስት መካከል የተደረገው የሰላም ስምምነት በሌሎች ክልሎችም መቀጠል ያለበት መልካም ጅማሮ መሆኑንም ኢሰመጉ ጠቁሟል፡፡

እንዲሁም መንግስት መንግስት የወጡ ሕጎችን በማክበር የሲቪክ ምህዳሩ እንዲሰፋና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ስራቸውን ያለማንም ጣልቃ ገብነት የሚሰሩበትን እንዲሁም የሲቪል ማህበረሰብ ሰራተኞችና መሪዎቻቸው በነጻነት ተንቀሳቅሰው እንዲሰሩ የሚያስችልና ከመሰደድ የሚጠብቅ ህግ እንዲያወጣ አሳስቧል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here