የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ከ13 ቢሊዮን ብር በላይ ያለማስያዣ ማበደሩን አስታወቀ 

0
163

ዓርብ ታሕሳስ 18 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ በሚቹ መተግበሪያ አማካኝነት ያለማስያዣ ከ13 ቢሊዮን ብር በላይ ማበደሩን አስታውቋል።

ባንኩ ከ750 ሺህ በላይ ለሆኑ የሚቹ ደንበኞች ያለምንም ማስያዣ ከ13 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር በመስጠት ከሁሉም ባንኮች ግንባር ቀደም መሆን መሆን መቻሉንም ይፋ አድርጓል።

የህብረት ስራ ባንኩ በሚቹ የፋይናንስ አቅርቦት አማካኝነት ለጥቃቅንና አነስተኛ የንግድ ተቋማት የንግድ ፈቃድና የብድር ማስያዣ ሳያስፈልጋቸው በቀላሉ የብድር አቅርቦት በማግኘት ላይ እንደሚገኙ ገልጿል።

ባንኩ ከዚህ ባለፈም ያለማስያዣ የሚሰጠውን ብድር ተበዳሪ ተቋማትና ግለሰቦች በቀላሉና በተያዘለት ጊዜ መሠረት በመክፈል ላይ እንደሚገኙ አስታውቋል።

የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ 6ኛውን የህብረት ሥራ ማህበራት ቀን  “የኅብረት ሥራ ማህበራት፣ ለሁሉም  የተሻለ ነገ አቅኚዎች” በሚል መርህ በዛሬው እለት በአዳማ ከተማ በደማቅ ስነስርዓት በማክበር ላይ ይገኛል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here