ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከነገ ጀምሮ ወደ ተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች ሊያቀኑ ነው

0
572

 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ከነገ ጀምሮ በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች ለሦስት ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት እንደሚያደርጉ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታወቀ።

በጉብኝታቸውን  ከ15 ሺህ ኢትዮጵያውያን ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ  የጽሕፈት ቤቱ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ ንጉሡ ጥላሁን ተናግረዋል፡፡

በተባበሩት ዐረብ ኢምሬቶች ከሚኖሩ እና ከመካከለኛው ምሥራቅ ከመጡ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር ውይይት እንደሚያደርጉም ኃላፊው ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት በመካከለኛው ምሥራቅ የሚኖሩ ዜጎች መብታቸው እንዲከበር የተለያዩ ተግባራትን በማከናወን ላይ ይገኛል ያሉት ንጉሱ፣ ከአገር ውስጥ ምቹ ሁኔታ ከመፍጠር ጀምሮ በሚኖሩበት አገር የሚገጥማቸውን ችግር ለመፍታት እየተሠራ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

ዜጎች ለሥራ ስምሪት በሕጋዊነት መንቀሳቀስ እንዲችሉ ከዮርዳኖስ፣ ኳታር፣ ሳዑዲ ዐረቢያ እና የተባበሩት ዐረብ ኢምሬቶች የሥራ ስምሪት ስምምነት መፈረሙን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ዐቢይ አህመድ  በሳዑዲ አረቢያ፣ ግብጽ፣ ሱዳን እና ሌሎች አገራት ቀደም ሲል ባደረጉት ጉብኝት በአገራቱ በእስር ላይ የነበሩ ዜጎች ከእስር ተፈተው እንዲመለሱ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡

የዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ ዙሪያ ትኩረት መድረጉን ተከትሎ እስካሁን ከ100 ሺህ በላይ ዜጎች ከተለያዩ አገራት ወደ አገራቸው መመለሳቸውን  ንጉሡ አመልክተዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here