ኢትዮጵያ በቅርቡ ለምትቀይራቸው የብር ኖቶች 3ነጥብ6 ቢሊዮን ብር ወጪ አወጣች

0
347

ኢትዮጵያ ለ23 ዓመታት ያህል  ስትጠቀምባቸው የነረበሩትን  የብር ኖቶችን መቀየሯ ይፋ ተደረገ።

በዚህም 262 ቢሊየን መጠን ያላቸው የብር ኖቶች የታተሙ ሲሆን ለህትመቱም 3ነጥብ6 ቢሊዮን ብር ወጪ መደረጉን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ ይናገር ደሴ (ዶ/ር) ለኢትይዮጵያን  ቢዝነስ ሪቪው መጽሔት (EBR) ገልጸዋል።

ነባሮቹን የ10፣ የ50 እና የ100 ብር የገንዘብ ዓይነቶች ሙሉ ለሙሉ በመተካት ለግብይት የሚሆን አዲስ የገንዘብ ዓይነት መጠቀም እንደምትጀምር  ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ  (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት ያስታወቁ ሲሆን የአምስት ብር ኖትም በጊዜ ሂደት በሳንቲም እየተተካ እንደሚሄድ አስታውቀዋል፡፡

ይህም አዲሱን የ200 ብር ገንዘብ እንደሚጨምር የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ፤  እነዚህ አዲስ የገንዘብ ዓይነቶች ለሕገ ወጥ እንቅስቃሴዎች የሚደረግን ድጋፍ፣ ሙስናን እና የኮንትሮባንድ ሥራዎችን ለመቀልበስ ይረዳሉ ተብሏል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here