ዳሽን ባንክ ፣ ኩዊንስ ሱፐር ማርኬት እና አዲስ ሆም ዲፖ በጋራ የግዥና የስጦታ ካርድ አዘጋጁ

0
1029

ዳሸን ባንክና በሚድሮክ ኩባንያ ውስጥ የሚገኙት ኩዊንስ ሱፐር ማርኬት እና አዲስ ሆም ዲፖ በጋራ በመሆን ዘመናዊ አመቺ ፣  አስተማማኝ ግብይት ለማከናወን የሚዉልና የሦስቱንም ኩባንያዎች መለያ የያዘና በተደጋጋሚ እየታደሰ በጥቅም ላይ ሊዉል የሚችል የግዥና የስጦታ ካርድ አቀረቡ፡፡

በሦስቱ ተቋማት በጋራ የተዘጋጀዉ ይህ ካርድ በህዝባዊና ሀይማኖታዊ በዓላት ወቅት እንዲሁም በምረቃና በሠርግ ወቅቶች ለተጠቃሚዎች የተለያዩ ስጦታዎች ይኖሩታል ሲል ዳሽን ባንክ ለአዲስ ማለዳ በላከው መግለጫ ላይ አሰታውቋል።

ይህም ማለት ደንበኞች ካርዱን ለተለያዩ ክፍያዎችና ግዥዎች በተደጋጋሚ በመጠቀም ነፃ ስጦታ እንዲያገኙ ስለሚያስችል ካርዱን አንዴ ከያዙ በኋላ በተደጋጋሚ እንዲሞሉና እንዲጠቀሙ ያስችለዋል ተብሏል፡፡

ካርዱ የክፍያ ካርድ ጭምር እንዲሆን በመታቀዱ የደንበኞችን የመጠቀም አቅም በማሳደግ ከምርት አቅራቢ ኩባንያዎችየሚፈፅሙትን የግዥ መጠን ለመጨመር እንደሚውልም ተገልጿል፡፡

ካርዶቹን ደንበኞች ለግብይት መጠቀም የሚችሉት በኩዊንስ ሱፐርማርኬትና በአዲስ ሆም ዴፖ የአግልግሎት መስጫማ ዕከላት ነው፡፡

በካርዱ ላይ የተጫነው የገንዘብ መጠን ሲያልቅ ከየትኛውም የዳሸን ባንክ ቅርንጫፍ በድጋሚ ገንዘብ በመጫን ካርዱን መጠቀም እንደሚቻልና ደንበኞች ካርዱን ለመጠቀም የባንክ ሂሳብ መክፈት አይጠበቅባቸውም።

 

 

 

 

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here