‹‹በ50 ዓመታት ከሠራነው ሰባት ዓመታት የሠራነው በጣም ትልቅ ነው››

0
854

ዑስማን ስሩር ባለፉት ሰባት ዓመታት የፌደራል ኅብረት ሥራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ። በትምህርት ዝግጅታቸው በልማታዊ ኮምንኬሽን ከታይላንድ የኹለተኛ ዲግሪያቸውን ሠርተዋል።

ትምህርታቸውን ጨርሰው ወደ ሀገር ሲመለሱ በሰለጠኑበት ዘርፍ የነበሩት ባለሙያዎች ቁጥር አምስት አይሞሉም ነበር። ዑስማን በታይላንድ ቆይታዬ በተለይ ከጃፓንውያን ፣ ኢንዶኖዢውያን፣ ከታዮች፣ ከፊሊፒኖች ጋር አብሬ በመማሬ ዜግነት ምን እንደሆነ በደንብ እንድረዳ አድርገውኛል ሲሉ ይገልጻሉ።

ስልጤ ዞን ግብርና ከተባለ ደግሞ ቀድሞ ሥማቸው የሚነሳው ዑስማን፥ “የሰው ልጅ ካመነ መሥራት ይችላል: ከቆረጠም ማሳካት ይችላል። ለብቻ የሚሠራ ሥራ የለም” በማለት የኅብረት ሥራ ዋናው ተልእኮም የኅብረተሰቡን ሁለንትናዊ እድገት ማበልጸግ ነው ሲሉ አጽንዖት ይናገራሉ። የአዲስ ማለዳው ዳዊት አስታጥቄ ከዑስማን ስሩር ጋር ያደረገው ቆይታ እነሆ..

ወደ ኀላፊነት ከመምጣትዎ በፊት እና በኋላ ስለኤጀንሲው በንጽጽር ቢገልጹልን
በመጀመሪያ ወደ እዚህ ኃላፊነት ከመመወጣቴ በፊት በደቡብ ክልል የኅብረት ሥራ ማኅበራት ኤጀንሲ ውስጥ ሰርተቻለሁ። ከዚያ በፊት ረጅሙን ጊዜ ያሳለፍኩት ግብርና ውስጥ ነው።ከወረዳ እስከ ክልል ድረስ በግብርና ጽ/ቤት እና ቢሮ ውስጥ በኀላፊነት ሰርቻለሁ።

አንዳንዱ ጉዳይ ለማነጻጻር ከባድ ነው።ትናንት የነበረበት እና ዛሬ ያለበትን ደረጃ ለማነጻጸር ሥር ነቀል ለውጥ አለ ብሎ መናገር ይቻላል።እኔ ስመጣ ኅብረት ሥራ ኤጀንሲ ሕንጻ ብቻ ያለው አንድ ግኡዝ ተቋም ነበር። ሥም ብቻ የነበሩ ስምንት ዳይሬክቶሬት የነበሩት ግን ተናብበው የማይሰሩ፣የጋራ እቅድ እንኳን ያላነበራቸው እንደ ተቋም ራዕይ አስቀምጠው የማይሰሩ ነበሩ። ተቋሙን በኋላፊነት ተመድቤ ሥራ ስጀምር መጀመሪያ ያደረኩት የመስሪያ ቤቱን አሰራር ለ ሦስት ወራት ማጥናት ነበር ። የውስጥ አመራር አንድነት ሳይኖር የውጪውን ማምጣት አይቻልም።

የኅብረት ሥራ ዋናው ተልእኮ ፣የኅብረት ሥራ ቤተሰቦችን ከድህነት አውጥቶ ሁለንተናዊ ብልጽግናን ማረጋገጥ ነው። ሁለንተናዊ ብልጽግና ሲባል ፖለቲካ አይደለም።ያስተሳሰብ እና የኢኮኖሚ ብልጽግና ማረጋጋጥ ነው።የኅብረት ሥራን ውጤት የምንለካው በገቢያቸው ማደግ ብቻ ሳይሆን ጤናቸው፣ደህንነታቸው የተጠበቀ ቤተሰቦችን መፍጠር በመቻል እና ለሌላውም አርአያ መሆን ሲቻል ነው።

ስለዚህ እኔ ከመጣሁ በኋላ የኅብረት ሥራ ኤጀንሲ ማኅበራት በቁጥር አድገዋል። ቁጥር መለኪያ ይሆናል እያልኩ ሳይሆን ከዚያ ጀርባ ያሉትን ጉዳዮች እናነሳለን። ከእኔ በፊት 38 ሺሕ ነበር ፣አሁን 92 ሺ ደርሷል። 38 ሺሕ ለመድረስ 22 ዓመታትን ፈጅቷል። እኔ ከተቀላቀልኩበት 7 ዓመታት ወዲህ ግን ከእጥፍ በላይ ጨምሯል።ኅብረት ሥራ የምታደራጀው በተደራጁ ፍላጎት ነው። ባንድ በኩል ፍላጎት መፈጠሩን የአባላት ቁጥር መጨመሩ ሲሆን ትልቁ ፈታኝ ጉዳይ ግን አምኖ መምጣጥ ነው።

እኔ ስቀላቀል የአባላት ቁጥር 6.7 ሚሊየን ነበር፡ ዛሬ 22.5 ሚልዮን ነው።ተጨማሪ ከ15ሚሊዮን አዲስ አባላት በ7 ዓመታትጊዜ ውስጥ ተቀላቅለዋል። ይህ የሚያሳየው መሥራት ብንችል ኖሮ እንደሚቻል ማሳያ መሆኑን ያመላክታል።በሌላ በኩል ስለ ካፒታል ስናወራ የማኅበራቱ ሀብት እና ንብረት ፣ኢንዱስትሪው፣ጥሬ ገንዘብ፣ተሸከርካሪው፣ሕንጻው፣ ተደምሮ የምናገኘው ሲሆን እሱም ቢሆን እኔ ስቀላቀል ፣በ2005 መጨረሻ 3.7 ቢሊዮን ብር ነበር።ዛሬ 28 ቢሊየን ነው።ለዚህ ነው እንዳንዱ ጉዳይ ለንጽጽር አስቸጋሪ ነው የምልህ።24.5 ቢሊየን አዲስ ሀብት በ 7 ዓመታት ጊዜ ውስጥ ማፍራት ተችሏል፡

ሌላው ቁጠባ ነው፣ አሁን ላይ 19.5 ቢሊየን ብር ደርሷል።ከ 18 ቢሊዮን ብር በላይ አዲስ ሀብት ማፍራት መቻሉ አሁንም እነዳለኩህ መሪ ከተገኘ ምን ያክል ጸጋ እንዳለን አመላካች ነው።ደግሞ ይህ 19 ቢሊየን ዝም ብሎ የተቀመጠ ሳይሆን ተመልሶ ወደ ኢኮኖሚው የሚገባ ነው።ያ ማለት ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጽእኖ ላይ የሚያመጣውን በጎ ተጽእኖ ማየት ይቻላል።እንደ አገር ሀብትን ሰብስቦ ሌላ ተደማሪ ሀብት መፍጠር መቻሉ በራሱ ሌላ ተልቅ አነርክቶ ነው።

ምርትን እሴት ጨምሮ መሸጥ እና የሥራ እድል ከመፍጠር አኳያ፣እና የውጪ ምንዛሬ ከማስገኘት አኳያ ምን ውጤት ተገኘተዋል?
በ2005 አመት አካባቢ 200 የነበሩትን ምርትን እሴት ጨምረው የሚያቀርቡ የኅብረት ሥራ ማኅበራት ቁጥር አሁን ላይ 971 የግብርና ማቀበባበያ ኢንዱስትሪ ደርሰዋል። ባለቤቶቻቸው አርሶ እና አርብቶ አደር የሆኑ ከትንንሽ እስከ ከፍተኛ ማለትም በቀን እስከ 15 ሺሕ ሊትር ዘይት የሚያመርቱ ኢንዱስትሪ ያሉዋቸው ማኅበራት የያዙ ናቸው።ከ 450 እስከ 1100 ኩንታል የስንዴ ዱቄት የሚያመርቱ ፋብሪካዎች ያሉዋቸው የኅብረት ሥራ ማኅበራት አሉ። ይሄ ማለት ከ አንድ እና ሁለት የሰው እስከ 30 እና 40 በላይ የሥራ እድል ፈጥረዋል ማለት ነው።

ከዚህም በላይ የውጪ ምንዛሬ ማስቀረትም ላይ አስተዋጽኦ አላቸው። ለምሳሌ ኢትዮጵያ ከውጪ የምታስገባውን ዘይት ከማስቀረት አንጻርም የአርሶአደሩንም ቴክኖሎጂ የመጠቀም ባህልን ያሳድጋል።በአጠቃላይ የብዜት ተጽእኖው ብዙ ነው።

እኔ ስመጣ የነበረው የሥራ እድል ፈጠራ 460 ሺሕ አካባቢ ነበር። ዛሬ 1.9 ሚሊዮን ደርሷል።ይሄ ቁጥር አንዳንዶቹን ሳናነሳ ማለት ነው፣ለምሳሌ አሁን ላይ እስከ 15 ሚሊዮን ኩንታል ማዳበሪያ በአመት ይገባል። እሱን የሚያራግፉ እና የሚጭኑ ሰዎች አሉ። ይሄ ጊዜያዊ የሥራ እድል ይፈጥራል ማለት ነው።
ዩኒየኖቹ 200 ብቻ ነበሩ፣ አሁን 391አካባቢ ደርሰዋል .ፌዴሬሽኖቹ ወደ አራት ናቸው።

አጠቃላይ የኅብረት ሥራ ማኅበራት ተግባራቸው ግብይት ነው። መዋቅር ተሰርቶ እንዲቀርብ አድርጌ አሁን እስከ ዞን ድረስ በዳይሬክቶሬት ደረጃ ተደራጅቶ እንዲሰራ ሆኗል።

ዋናው የኤጀንሲው ተልእኮ ገበያ ማገበያት ነው።በአገር ውስጥም በውጭም፣አሁን ላይ የኅብረት ሥራ ማኅበራትበግብርና ምርቶች የግብይት በአማካይ ድርሻ 15 በመቶ ነው። በምርት አይነት ከወሰድነው ግን የለያል።ለምሳሌ አትክልት እና ፍራፍሬ ብንወስድ እስከ 50 በመቶ ይደርሳል።

በውጪ ገበያ ተሳትፎንም በተመለከተ ያኔ በቡና ብቻ ተወስኖ የነበረው አሁን ላይ 50 የሚደርሱ ማኅበራት ምርቶቻቸውን ወደ ውጪ የሚልኩ ሲሆን ዋናነትም ሰሊጥ እና ቡና ሌላ ጥራጥሬ፣ ማሾ፣ ማር በተወሰነ መልኩም ቢሆን አትክልት እና ፍራፍሬ በመላክ የሚያመጡት ገቢ በጣም ከፍተኛ ነው።ይሄ እንግዲህ ለአገርም ትልቅ አስተዋጽኦ አቅም ነው።

እንደ አጠቃላይ በኅብረት ሥራ ትላንት እና በኅብረት ሥራ ዛሬ ያለው ልዩነት በሴቶች፣ በወጣቶች ተሳትፎ እና አመራርነት ማድጉ እርግጥ ነው። ቅድም ከጠቀስኩት አጠቃላይ አባላት ቁጥር ውስጥ 32.7 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች ናቸው።ያኔ ወደ 15 በመቶ አካባቢ ነበር የነበረው። ስለዚህ ሴቶች ከኅብረት ሥራ አንጻር የተለየ ተልእኮም ስላላቸው አካሁዱ ጥሩ የሚባል ነው። ኅብረት ሥራ የብዙሃን ሐብት ነው።በመሆኑም እንደዚህ ዓይነት ማሕበራት በጣም ኀላፊነት በሚሰማቸው ሰዎች፣ በእኔነት ስሜት ካልተመራ ለአደጋ ይጋለጣል። ሥለዚህ የኅብረት ሥራ ማኅበራት በአባላት ቁጥር፣በሴቶች ፣በወጣቶች ተሳትፎ፣በካፒታል፣ በቁጠባ ፣በኢንዱስትሪ፣ በሜካናይዜሽን እና በሌሎች መስፈርቶች ሲታይ ትልቅ እምርታ አለው።

ሃምሳ ዓመታት ከሰራነው 7 ዓመታት የሰራነው በጣም ትልቅ ነው። ነገር ግን ኢትዮጵያ ካላት ጸጋ ፣ኅብረተሰቡ ጋር ከተፈጠርው ፍላጎት፣ መንግስትም ሆን ባለድርሻ አካላት ከእዚህ ሴክተር ከሚጠብቀው ውጤት እና የኅብረት ሥራ ማኅበራት ሌላ ዓለም ከሚያበረክቱት አስተዋጽኦ አንጻር ግን ለእኔ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፣ገና ብዙ ይቀራል።

የኅብረት ሥራ ማኅበራት ኤጀንሲ የተቋቋመበት ዓላማ ምንድን ነው? ምን ያክልስ ዓላማውን አሳክተል?
እኔ ከአላማው አንጻር በጣም ስኬታማ ነው ብዬ አስባለሁ።ለእኔ ለስኬታማነቱ መነሻ ፖሊሲ ፣አዋጅ፣መመሪያ ማዘጋጀት ፣ የገበያ ትስሥር መፍጠር አቅም መገንባት እና አስተሳሰብ ላይ መሥራት ነው። ገበያውን እስከ አለም አቀፍ ገበያ ድረስ ዘልቆ እንዲገባ የማስተዋወቅ ሥራዎችን በመሥራት ሁለንተናዊ ድጋፍ ማድረግ ነው። ከዚህ አንጻር አሁን ባነሳኃቸው ሁሉ ሥራዎቹን አሳክቶ ሰርተል፡፤

ለምሳሌ የኅብረት ሥራ ማኅበራት አሁን ከደረሱበት የእድገት ሥራ አንጻር፣ የሚመጥን አዋጅ አውጥቶ አጸድቋል፣ አዋጁን ተከትሎ ሊወጡ የሚገባቸው መመሪያዎች አሰራሮች ተዘርግተል። የኅብረት ሥራዎቹ አሁን ያሉበትን ሁኔታ አግናዝቦ ወደ ፊት ሊመሩበት የሚገቡ ፖሊሲዎችን አዘጋጅተል። የ 15 ዓመታት ፍኖተ ካርታም አዘጋጅተዋል። አሁን ይህን ማዘጋጀት ብቻ አይደለም፣ሁሉንም ሥራዎች የሰራው የውስጥ አቅሙ ገንብቶ ነው። ኅብረት ሥራ ለእኔ ይጠቅመኛል ብሎ እየመጣ ነው።
ለዚህም ቁጥሩ ማሳያ ነው።እንደውም አሁን ላይ አዲስ ከማደራጀት ይልቅ ማጠናከር የሚለውን አካሄድ እየተከተል ነው። ኅብረተሰቡ ውስጥ የነበረው ሁኔታ ሰው እንዳይመጣ የሚገፋ ነበር።በህብተሰቡ ውስጥ ያለው የተጠቃሚነት ደረጃ እየሰፋ ስለመጣ ገፊ ሳይሆን ሳቢ እንዲሁን አድርጎታል።እንደ አጠቃላይ የኅብረት ሥራ ኤጀንሲው ውጤታማ ነው፣ለዚህም ከቁጥርቹ ጀርባ ያለውን ጉዳይ ነው የማነሳው።ግን ገና ብዙ ይቀራል።የኅብረት ሥራ ማሕበራት ስኬት ሃዲድ ውስጥ እንደገባ ባቡር ነው ።አንዴ ገብተል ፍጥነቱን በመጨመር ውደ ፊት እንዲሄድ ማድረግ ነው።

ለምንድነው የኅብረት ሥራ ማኅበራት ወደ ሌላ ምእራፍ መሸጋገር አለባቸው ያሉት
እኔ እንግዲህ እዚህ ተቋም ስቀላቀል የቁጠባ እና የካፒታል መጠኑን በመደመር 5 ቢሊየን አካባቢ ነበር። ዛሬ 48 ቢሊየን ደርሷል። ይሄን የሚያስተዳድር ፣የሚመራ፣የሚያስተዳድር የሚከታተል የሚደግፍ ጠቋማዊ አደረጃጀት የሰው ሀይል እና አሰራር ያስፈልጋል።ስለዚህ አሁን ላይ ማብቂያው ነው ባልልም ሁሉም ነገር የእድገት ምእራፍ ስላለው የእይታ ለውጥ ፣የአደረጃጀት ለውጥ፣መምጣት ይገባዋል።

የፌደራል ኅብረት ሥራ ኤጀንሲ በተለይ መንገድ የኅብረት ሥራ ማኅበራት ሪፎርም በመከተል እንደሚገባ ሥምምነት ተነስልቷል ምን ማለት ነው?
የዛሬ የኢትያጵያ ኅብረት ሥራ ማኅበራት የደረሱበት የእድገት ደረጃ አለ። የእድገት ደረጃው በማኅበራት ቁጥር፣ በአባላት ብዛትና በፈጠሩት ሀብት ወ.ዘ.ተ አሁን የሉት የኅብረት ሥራ ማኅበራት በደረሰበት ደረጃ በአሰራር፣ በአደረጃጀትና በሰው ሀይል ልክ ካልተደራጀ ባለበት ቆሞ ይቀራል ። ስለዚህ ዛሬ የኢትዮጵያ ኅብረት ሥራ ማኅበራት በደረሱበት ደረጃ ልክ መደራጀት ያፈልጋል።

የኅብረት ሥራ ሴክተሩ አድገቱ በህብረተሰቡ፣ በመንግስትና በተቋማት በኩል ፍላጎቱ እያደገ ነው። በመሆኑም አሁን ያለውን ፍላጎትና እድገት ያገናዘበ ተቋማዊ አደረጃጀት ያስፈልጋል። ተቋማዊ ለውጡ በተጠናከረ ደረጃ ሲገነባ አሁን ያለውን የመንግስትን፣ የአባላትንና የህብረተሰቡን ፍላጎት መመለስ ይቻላል። አሁን ላይ በኢትዮጵያ ካሉት ኅብረት ሥራ ማኅበራት ውስጥ 50 ዎቹ ምርታቸወን ለዓለም ዓቀፍ ተቋማት እያቀረቡ ነው። እነዚህ ማኅበራት ምርታቸውን ለውጭ ገበያ ሲቀርቡ ዓለም ዓቀፍ ከሆኑ ድርጅቶች ጋር ነው የሚወዳደሩት። ስለዚህ የነዚህን ማኅበራት አቅምና ተወዳዳሪነት ለማጎልበት በአሰራር፣ በአደረጃጀትና በሰው ሀይል በተሻለ አቅም ማደራጅት አስፈላጊ ነው።

ውጤታማ ሆነ አደረጃጀት ለመፍጠር አሁን በተለያያ ደረጃ ላይ ዩኒየኖች 92 ሺሕ ኅብረት ሥራ ማኅበራት በየደረጃ እና በየዘርፉ ማደራጀት ይጠይቃል። ከ92 ሺሕ ማኅበራት በዓመት ከ 1.5 አስከ 3 ቢሊዮን ብር የንግድ እንቅስቃሴ የሚደርጉ አሉ። በአንጻሩ ደግሞ በዓመት ከ10 ሺሕ አስከ 20 ሺሕ ብር የሚንቀሳቅሱ አሉ። እንዚህን እንደየ ሥራ ዘርፋቸው ከፍተኛ፣ መካከለኛ፣ ዝቅተኛና ከዝቅተኛ በታች ብሎ በደረጃ ማስቀመጥ አንዱ የሪፎርሙ አካል ነው።

አደረጃጀቱን የሚጠናክር መመሪያ ማዘጋጀት ደግሞ የአደረጃጀቱን መረጃ በሚመጥን መልኩ ማዘጋጅት። በሰው ሀይል በኩል እያንዳንዱ ሰራተኛ በሰራው ሥራ ልክ ተጠቃሚ ማድረግ ተገቢ በመሆኑ በሪፎርሙ የሰራተኛ ደመወዝና ቦነስ በሪፎርም ይካተታል።ሌላው ማኅበራት በሳይንሳዊ አሥራርና በሙያተኛ መመራት አለባቸው።

ከኅብረት ሥራ ማኅበራት አማካኝነት ምንያክል የውጪ ምንዛሬ ተገኝተዋል
ከጊዜ ወደ ጊዜ እድገትን እያመጣ ነው፣ ዘንድሮ አሁን በነበርንበት በኮቪድ ወቅትም ቢሆን ከ98 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚሆን የውጪ ምንዛሬን አስገኝተዋል። ይሄ በርግጥ በእኛ ግምገማ በቂ ነው አንልም። 50ዎቹም ማኅበራት ኤክስፖርት ውስጥ ገብተዋል 35ቱ አመቱን በሙሉ በተከታታይ የሰሩ ናቸው። ሌሎቹ ጋር ገባ ወጣዎች አሉ ማለትም ገበያ ውስጥ አለመቆየት ተዘርሮ ተመልሶ ምርታቸውን በመሰብሰብ ወደ ኢ-ሴክስ የማስገባት እንዲህ እንዲህ አይነት ነገሮች አሉ። ይሄ ነው እኛንም ወደ ሪፎርሙ እንድንገባ ያደረገን ከእድገቱ ባሻገር እንዲህ አይነት ገበያው ውስጥ አለመቆየትይገጥማል።

በአመቱ አሁን ከ198 ሚሊየን ዶላር በላይ የውጪ ምንዛሬ ገቢ አስገኘተዋል። የውጪ ምንዛሬ ስንል ከመጠኑ ባሻገር ምርቱ መጀመሪያውኑ ሲሰበስቡ አርሷአደሩ የተሻለ ዋጋ እንዲያገኝ ያደርጉታል።፡ ለምሳሌ ቡና እነሱ በመኖራቸው ምክንያት በአንድ ኪሎ አራትና አምስት ብር ተጨማሪ እንዲያገኝ ሆንዋል ይሄ ብቻ ሳይሆን እነሱ በመክፈላቸው ሌላውም አካል ይከፍላል ይሄ አንድ የራሱ የሆነ ፋይዳ አለው። ሁለተኛ ደግሞ እዛ የሚሸጡበት ዋጋ የ20 እና 30 በመቶ የዋጋ ልዩነት አለ። ይሄ እንደ አገር የውጪ ምንዛሬ ግኝታችን እና ለምርታችን ተወዳዳሪነት እንዲሁም በጥራት ምርትን በማቅረብ ገፅታን በመገንባት የራሳቸው የሆነ ሚናን ይጫወታሉ።

የአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጠና ሥምምነት ሒደት ላይ ትገኛለች ከአፍሪካ አገራት ጋር ግብይት ለማድረግ የኅብረት ሥራ ማኅበራት ዝግጅት ምን ይመስላል?
አንግዲህ የአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጠና ዝግጅት ለምርጫ የሚቀርብ ጉዳይ አይደለም። ራስን አዘጋጅቶ በዛ ውስጥ ተጠቃሚነትን ከፍ ለማድረግ መሥራት ይጠይቃል። አንዳንድ ዝግጅት የጀመሩ ማኅበራት አሉ። ያን ለማድረግ ዝግጅቱ በዋናነት ተቋማዊ የማስፈፀም አቅምን ማሳደግ ነው። ተቋማዊ የማስፈፀም አቅምን ስንል ምንድን ነው? ቅድም ያነሳኋቸው ሶስት ጉዳዮች ይሄን ይመልሱታል።

በነገራችን ላይ አደረጃጀቱም፣ አሰራሩም የሰው ሀይሉም አንዱ ተቋማዊ የማስፈፀም አቅምን ማሳደጊያ ነው። ሌላው መሰረተ ልማት ነው። ለምሳሌ ንግድ ቀጠና ውስጥ ሲገቡ ምርትን በመጠንም፣ በጥራትም በዋጋም ተወዳዳሪ መሆን አለባቸው። ሶስተኛው በምርት ዱካ መታወቅ አለባቸው። በምርት ዱካ ስንል የቤኒሻንጉሉን ማር የቤኒሻንጉሉን ቡና በአካባቢው ላይ ተመሥርቶ ዱካው የሚታወቅ ምርት ይዘው መሄድ አለባቸው።

ይህን ለማድረግ ደግሞ መደመር አለባቸው። ለዚህም መሰረተ ልማቶች መሟላት አለባቸው። ስለዚህ እነዚህን ጥያቄዎች የሚመልስ ሥራ መሥራት ይገባናል። ይህን የጀመሩ አሉ ለምሳሌ ቤንች ማጂ አንድነት የሚባል እንዲሁም ሌሉች ጥቂት ማኅበራት የጀመሯቸው ሥራዎች አሉ ግን ሰፊ ሥራ ይጠይቃል። ቅድም እንዳነሳሁት ተቋሙ የደረሰበት ደረጃና ሰዉ እይታ ማኅበራቱ ውስጥ ያለው የሰዉ ሀይል፣ አደረጃጀት ወደ እዚህ የሚጋብዝ አይደለም።

ስለዚህ ይሄን ከመሥራት አኳያ አሁን ሪፎርሙ መልስ ይሰጠዋል ብለን እናስባለን። ዝግጅቶች ግን ውስንነት ቢኖረውም እዚም እዛም የተጀማመሩ ነገሮች አሉ። ለምርጫ የሚቀርብ ጉዳይ አይደለም። ተጠቃሚነትን እናሳድግ ካልን የእኛ ዋናው የገብያ ማእከላችን ደግሞ አንዱ አፍሪካ ሊሆን የሚችልበት እድል ይኖራል፤ ካለን ፀጋም አንፃር ተጠቃሚ ነው የምንሆነው እንደ አገር ነው።

የኅብረት ሥራ ማኅበራት ሒሳባቸውን IFRS international Finanacial Reporting System እንዲሰሩ በኢትዮጵያ አካውንቲንግ እና ሂሳብ ቦርድ የተቀመጠው አቅጣጫ ምን ደረሰ?
እዚህ አካባቢ ስንመጣ አንዱ ችግር ብለን የለየነው የሂሳብ አያያዝ ሥርአቱ በተለይ የሌሎቹን ሁኔታ የሚገልፅ ባይሆንም በዋናነት ማኅበራት ጋር የሂሳብ አያያዝ ላይ መሰረታዊ ችግር አለ፣ ለ አይ.ኤፍ.አር.ኤስ እራስን ከማዘጋጀት ጋር ችግር አለ። ስለዚህ አንዱ ሪፎርሙ የሚመልሰው ተቋማቱ ባላቸው የደረጃ ልክ እነዚህን ችግሮች ከመፍታት አንፃር መሰራት ያለባቸውን ሥራዎች አሉ። ለአይ.ኤፍ.አር.ኤስ እራስን ከማዘጋጀት አንፃርም ለምርጫ የሚቀርብ ጉዳይ አይደለም። ስልጠና ሰጥተናል እኛ ከኦዲት ቦርድ ጋር ሆነን ባለፉት ሁለት ሶስት አመታት የጀመርናቸው ሥራዎች አሉ። እንደውም በዚህ አመት ብዙዎቹ ይገባሉ ብለን ነበር። ግን አሁን ባልኩት የማስፈፀም አቅም ጉድለት እዚያ ጋር ያለው የሰው ሀይልም፣ አሰራርም፣ አደረጃጀትም እነማን ይግቡ ብለን ስንል ለምሳሌ ከፍተኛ ደረጃ ብለን የምንፈርጃቸው ውስጥ የሚወድቁት በቀጥታ ወደ ኤይ.ኤፍ.አር.ኤስ ሥርዓት ይገባሉ።

ቀጥሎ ደግሞ መካከለኛ የሚባሉት ኢንኩቤት እያደረጉ እነሱን እየገራን ወደዚህ ሥርዓት እንዲገቡ እናደርጋለን ለምርጫ የሚቀርብም አይደለም።አሁን ብድር ለማግኘት ምን ለማለት ይሄ ኤይ.ኤፍ.አር.ኤስ ውስጥ መግባት በጣም ትልቅ ተጠቃሚ ያደርጋቸዋል። ምክንያቱም ግልፀኝነትን ያሰፍናል በቀላሉ ማግኘት ይችላል።

በአዲስ አበባ የኑሮ ውድነት እና የ ሸቀጦችን ዋጋ ለማረጋጋት የተሰራው ሥራ ምን ደረጃ ደረሰ? ምን ውጤት አስገኘ?
በአዲስ አበባ ላይ ብቻ ሳይሆን በመላው ሀገራችን ከ ጥንስስ ከተሞች እስከ አዲስ አበባችን ባለው ኅብረት ሥራ ማኅበራቱ ሰው ሰራሽ ኑሮ ውድነቱን ኢኮኖሚያዊ ምክንያት የሌለውን የምርቶች ዋጋ መጨመርን ለመከላከል ሰፊ ሥራ ሰርቷል። በዚህም አንደኛ የመከላከል ሁለተኛ ተጽኖውን መቀነስ ጉዳይን በስፋት ተሳትፈው የኅብረት ሥራ ማኅበራት በተጨማሪም የህዝብ አለኝታ የህዝብ ተቋም ለክፉ ቀን ደራሽ ተቋም መሆናቸውን አስታውቀዋል።በአዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን በመላው ሀገራችን ከትላልቅ እስከ ትናንሽ ከተሞች ገጥመዉት የነበሩትን የፋይናንስ አቅርቦት ችግር ነበር።

ይሄንን ችግር ለመፍታት ደግሞ በመንግስት በኩል የብድር ፕሮጀክት ሁለት ቢሊየን ብር ጠይቀን ሥምንት መቶ ሚሊየን አካባቢ ተፈቅዶ ለሰማኒያ ሰባት ማኅበራት ብድር ተመቻችቶ ወደ 47 ማኅበራት መመዘኛዎችን አሟልተው ከ ሶስት መቶ በላይ ብድር ወስደዋል። ወደ 34 ማኅበራት ብድሩን ተይቀው የ ብድር ፎርማሊቲውን ማሟላት ባለመቻላቸው እስካሁን ብድሩን አልወሰዱም። ነገር ግን ብድሩ የአመት ብድር ስለሆነ ይቀጥላል በ ሒደት ላይ ያሉ 4 ማኅበራት አሉ።የኑሮ ውድነቱን በ መከላከል ረገድ ትልቅ ለውጥ የመጣበት ሁኔታ ና ለህብረተሰቡ እፎይታ የሆነበት ሁኔታ ነበረ።

በተለይም ሙሉ በ ሙሉ በተዘጋባቸው ቦታዎች ለምሳሌ ባህር ዳር እንጂባራ ከተሞች ላይ ኅብረት ሥራ ማኅበሩ ቤት ለቤት ምርቶችን ሲያቀርቡ ነበር። በዚህም ማኅበራቱ በ ኮቪድ 19 ምክንያት ህብረተሰቡ ላይ ይፈጠር የነበረውን ሰው ሰራሽ የ ኑሮ ውድነቱን ከመቀነስ አኳያ የማይተካ ሚና ተጫውተዋል።

በአዲስ አበባ የግብርና ምርቶች የገበያ ማእከላት ጉዳይ ላይ በ አዲስ አበባ ዋና ዋና በሮች ላይ የግብርና ምርቶች በ ቀጥታ ከ አምራቹ አስገብቶ በጅምላ በችርቻሮም ለሚሸጡ አካላት የሚል ፕሮጀክት ቀርጸን ቀድሞ ለነበሩት ክቡር ከንቲባ አቅርበን ምላሹን እየጠበቅን ነዉ። ፕሮጀክቱ ለ ሁሉም አካል ጠቃሚ ነው።

እንደ አጠቃላይ በዐሥር ዓመት እቀድ ውስጥ በዋናነት ምን ሊሰራ ታስቧል? በያዝነውስ ዓመት?
የዐሥሩ ዓመት መሪ እቅዳቸን ዋናው አቅጣጫ አምስት መስረታዊ ጉዳዮች ላይ አተኩረን በመሥራት የኢትዮጵያ ኅብረት ሥራ ማኅበራት የኅብረት ሥራ ቤተሰቦችን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር በዘላቂነት ሊፈቱ ይገባል የሚል ነው። በሚቀጥሉት ዐሥር ዓመታት የኅብረት ሥራ ቤተሰቦች በመሰረታዊነት ኑሮቸው የተቀየረ መሆን አለበት። ይሄን ለማድረግ አምስት መሰረታዊ የትኩረት መስኮች ተለይተዋል።

አንደኛው ኅብረት ሥራ ማኅበራትን ማጠናከርና ማዘመን ይህም በአደረጃጃት፣ በአሰራር፣ በልምድ እንዲመሩ ማድረግ ሲሆን ሁለተኛው የኅብረት ሥራ ማኅበራት የሃገር ውስጥም ሆነ የውጪ የገበያ ድርሻና ተሳትፎ ማሳደግ ነው።በሀገር ውስጥ የሚደረግ ግቢይትን 60 በመቶ እና የውጭ ግብይትን 10 በመቶ በኅብረት ሥራ ማኅበራት ሥር ማድረግ ሶስተኛው የግብርና ምርትን በጥሬው ከማቅረብ በተጨማሪ ዕሴት ጨምሮ ለገበያ ማቅረብ ይህን ለማድረግ ነባር ኢንዱስትሪዎችን ማሳደግና ማስፋፋት አራተኛው ደግሞ የኅብረት ሥራ ማኅበራት ቁጠባ መጠንን መጨመር ሲሆን አምስተኛውና እና ዋነኛው የኅብረት ሥራ ማኅበራትን ህጋዊነትንና ደህንነትን ማስጠበቅነው።

ቅጽ 2 ቁጥር 102 ጥቅምት 7 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here