‹‹አየር ኃይላችን ጠላት ሊጠቀምባቸው ያሰባቸውን ምርጥ ኢላማዎች በመደብደብ ከጥቅም ውጭ አድርጓል›› ሜጀር ጄነራል ይልማ መርዳሳ

0
1246

የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጄነራል ይልማ መርዳሳ ዛሬ ህዳር 02/2013 በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ‹‹ለጁንታው እስትንፋስ የነበሩ የነዳጅ ዴፖዎች ፣ የመሳሪያ ማከማቻዎች እና ሌሎች ምርጥ ኢላማዎችን ጀቶቻችን ያለምንም ከልካይ እንዳሻቸው እየተመላለሱ አውድመዋቸዋል›› ብለዋል ።

ፓይለቶቻችን የተመረጡ ዒላማዎችን ለመደምሰስ መሣሪያ ጭነው እየሄዱ ሲቪል የሚጎዳ ከመሰላቸው ሳይተኩሱ በመመለስ ነጥሎ የመምታት ስትራቴጂ እየተከተሉ ይገኛሉ ሲሉ በመግለጫቸው ላይ አስታውቀዋል ።

‹‹ጁንታው እንመታለን የሚለው ፣ እድሜውን ሲዋሽ ስለኖረና እየዋሸ ስለሚቀበር ባህሪው ነው›› ያሉት ሜጀር ጀነራል ይልማ ‹‹ ባሻን ሰዓት እየተመላለስን ለህግ እስኪቀርብ ማጥቃታችንን እንቀጥላለን›› ማለታቸውን የመከላከለያ ሠራዊት በፌስቡክ ገጹ ላይ አስፍሯል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here