በአዲስ አበባ ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ከአራት ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የአደንዛዥ እጽ በቁጥጥር ስር ዋለ

0
918

በኮልፌ ቀረንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 በተለምዶ ቄሶች ሰፈር በሚባለው አካባቢ በህብረተሰቡ ጥቆማ የተለያዩ አደንዛዥ እፆች ሺሻ እና የተለያዩ ሲጋራ በቁጥጥር ስር መዋሉን የኮልፌ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ዋና ሃላፊ ኢንስፔክተር ሃብታሙ አንተነህ ገልጸዋል ።

አደንዛዥ እፁ የተገኘው አዲስ እየተሰራ በሚገኝ ፎቅ ቤት ምድር ቤት መሆኑን የተናገሩት ኢንፔክተር ሃብታሙ የአካባቢው ማህበረሰብ በሰጠው ጥቆማ እና በተደረገ ፍተሻ እፁ ሊያዝ ተችሏል ብለዋል።

በቁጥጥር ስር የዋለው አደንዛዥ እጽ ከውጭ ሀገር በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ሀገር ውስጥ የገባ መሆኑን ገልፀው ወደ ህብረተሰቡ ሳይሰራጭ መያዙ በህብረተሰቡ ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት ለማስቀረት መቻሉን ኢንፔክተር ሃብታሙ ተናግረዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here