ጦርነቱ ሲጠበቅ የነበረ ወይንስ ድንገት የተፈጠረ ክስተት?

በጦርነት ላይ ቤንዚን እያርከፈከፈ የሚገኘው የማኅበራዊ ሚዲያ ሌላኛዉ የጦር ቀጠና።

ኢትዮጵያ ከሰሞኑ እያስተናገደች ያለችው  ሁነት የብዙሃኑን ልብ የሰበረ ጉዳይ ነው፡፡ዱር ቤቴ ብሎ ከቤቱ እርቆ የአገርን ዳር ድንበር በማስከበር ላይ ባለ የጦር ቡድን  ላይ በተሰነዘረው  ጥቃት ያልተከፋ ዜጋ የለም፡፡በርግጥ ይህ ጉዳይ የድንገት ወይስ የቆየ ቀጠሮ ነው?የሚለን ቤተኛችን ጋዜጠኛ ሳዲቅ ጁሃር ነው መልካም ቆይታ

ማኅበራዊ ሚዲያ በዋናነት የተቋቋመው የሚዲያ ተደራሽነትን እና ክፍተትን ለሟሟላት ሲሆን ለጭቁኖች ድምፅ በመሆን ተአማኒ ገለልተኛ በሆነ መልኩ ሐሳብን በነፃነት ለመግለፅ ያለመና ለማኅበረሰቡም ጭምር ለማጋራት ለማንቃት ነው አላማው። ከዚህ በተጨማሪ ዓለም ወደ ቴክኖሎጂ ባደገችበት በዚህ ወቅት ዲጅታል ሚዲያው በቀላሉ ንግድ ለመስራት ለማስተዋወቅ …..አንደኛው ዓለም ከሌላኛውም ለማስተሳሰር ታልሞ የነበረ ቢሆንም በዋናነት ግን ማኅበራዊ ሚዲያው በተለያዩ አገራት ሕዝብን በማንቃት በኩል ከፍተኛ ፖለቲካዊ ሥራ ሰርቷል።

የአረብ ፀደይ ተቃውሞ እና በአገራችንም ለህውሃት መንበርከክ ወጣቶች በቀላል መረጃ ለመለዋወጥ ይረዳ ስለነበር ጉልህ ሚና ተጫውቷል ሆኖም ከሪፎርሙ ወዲህ ማኅበራዊ ሚዲያው ድንጋይ መወራወሪያ ጥላቻ መስበኪያ በለው በለው የበዛበት ሆኖ እዚህ ዘልቋል። በማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀማችን እጅግ የወረደ ከመሆኑ ጋር አለቅላቂ ተደጓሚ ካድሬ የበዛበት የጨቀየ መድረክ ሆኗል። ሰሞኑ ደግሞ በመከላከያ ሰራዊቱና በህውሃት መካከል የተፈጠረው አለመግባባት በማጋጋል አገሪቱ ከገባችበት ፖለቲካዊ ቀውስ እንዳትወጣ እዚህም እዚያም ያሉ ሰዎች ቤንዚን በማርከፍከፍ ትልቅ ሚና ተጫውቷል።

 ጦርነት የሚደረግበት ቦታ ሳያዩ ሣይሄዱ ጭምር የመሰለኝ የውሸት ዘገባዎችንም ማኅበረሰቡንም ግራ ግብት አድርገው ኮንፊውዝ ሲያደርጉት አስተውያለሁ ።የሚገርመው የማኅበራዊ ሚዲያውን ወጀብ ተከትለው የሚነጉዱ ምሁራን ሰዎችም በሚዲያ እየመጡ ጭምር መባል የሌለበት ነገር ሲሉም ተስተውሏል። ይኸውም ጦርነቱ የድንገት የተከሰተ ተአምር አድርገው ሲያቀርቡም በደመነፍስ እየተጓዘ ያለ ጭፍራ መኖሩ ግርምት ጭሮባኛል።

 እኔም ስል እጠይቃለሁ ጦርነቱ ሲጠበቅ የነበረ ወይንስ በድንገት የተከሰተ ? እኔ አሁን በመከላከያ ሠራዊቱና በህውሃት መካከል እየተደረገ ያለው ጦርነት በቀላል አማርኛ ድንገት የተከሰተ ሳይሆን ሲጠበቅ የነበረ በኹለቱም በኩል ዝግጅት የተደረገበት ሁነት መሆኑ ከበርካታ መረጃዎቼ ጋር አያይዤ ለማቅረብ እወዳለሁ ።

 በመጀመሪያ አሁን በስልጣን ያለው የብልፅግና ፓርቲ ለአስራ ሰባት ቀን በተደረገ ዝግ የፖለቲካ ድርድርና ቃል ኪዳን በኋላ ነበር ወደ መንበረ ስልጣኑ የመጣው። ላስታውሳችሁ…፤ በኹለቱ ወገኖች መካከል ስለተደረገው ዝግ ውይይት ምን እንደሆነና በምን ላይ ተስማምተው እንደወሰኑ እስካሁንም በኹለቱም በኩል ያሉ ሰዎች ግልፅ ማድረግ አልፈለጉም እኔ ይህንን ያልኩበት ምክንያት ህውሃት ያለምንም ቅድመሁኔታ ስልጣኑን አስረክቧል የሚለው አሳማኝ አይደለም ።ስለማይሆንም ነው።

ስለዚህ በኹለቱ ፓርቲዎች መካከል ስለተደረገው ስምምነት መከዳዳት ወይንም ስምምነቱን መፍረሱ አመላካች ነገሮች ነበሩ በዚህ መሰረት የመጀመሪያው ተቃርኖ እዚህ ጀምሯል ማለት ይቻላል።  ለምሳሌ የፓርቲ ስም መቀየር ርእዮተ ዓለም መቀየር፤ ..ጥፋት በፈፀሙ የህውሃት አባላት ላይ የወጣው ባቻየእስር ትእዛዝ ማውጣት፤…የኹለቱ ፓርቲዎች….ትዳር ወደ ፍቺው እንዲያቀና የገፉት ሁነቶች ናቸው ማለት ይቻላል።

ታዲያ ኹለቱ ወገኖች ቅድመ ሁኔታ አስቀምጠው የነበረ ይመስላል የተስማሙት  ምክንያቱም የኦሮሚያ ርእሰ መስተዳደር ከዛም የመከላከያ ሚኒስተር አቶ ለማ መገርሳ ከላይ ባሉት ነገሮች ባለመስማማታቸው ያሰሙት ተቃውሞ ዝም ብሎ ከመሬት የተነሳ ነበር ብሎ ለማለት ይከብዳል ። ህወሃቱም ቢሆን አዲሱ ፓርቲ እያዋቀረው ያለው የአብይን ስርዓት በመቃወም ለብቻው በመነጠል ማዕከላዊ ከተማውን ለቆ ትግራይ ለመክተም ተገደደ።

 ……እናም ታዲያ ከዚህ ግዜ በኋላ የህውሃትና የፌደራል መንግሥት ግልፅ የቃላት ጦርነቶች ውስጥ መግባታቸው የረሳው ካላ …….ይኸው ለማስታወስ ነው  አንዳንዶች አሁን በፌደራል መንግስቱና በህውሃት መካከል የሚደረገው ጦርነት ድንገት የተፈጠረ ሲያስመስሉት እነዚህ እዚህ አገር ላይ አልነበሩም …..እንድል ያስገድደኛል።

ምክንያቱም ከላይ እንደገለፅኩት ከሽግግሩ ግዜ አንስቶ በኹለቱ አካላት መካከል የሚደረገው የቃላት ጦርነት ወደ ሪል ጦርነት እንደሚያመራ መገመት የኹለቱን ሁኔታ ለተከታተለ ሰው አዲስ አይሆንበትም/የጦር ተንታኝም መሆን ዓይጠበቅበትም ….አንድ ባንድ እንያቸው ካልንም …..

ለአገር አንድነት ሲባል በከተማችን በየሳምንቱ እሁድ በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተለያዩ መረጃዎችን ወደ ሕዝብ የምታደርሰው ፎርቹን ጋዜጣ (vol 21 no 1071 nov 8/2020 )POINT OF NO RETURN ብላ ባወጣችው እትም የህውሃትና የፌደራል መንግሥቱ እንካ ሰላንቲያ ከየት ጀምሮ የት ላይ እንዳበቃ ያቀረቡትን ግራፍ ጠቃሚ ስለሆነ እኔም ወደ አማርኛው ከርበት አድርጌ አዋዛዋለሁ። …….

ፎርቹን ጋዜጣ የህውሃትና የፌደራል መንግሥት የዋላት ጦርነትና መጠዛጠዝ በሲኩዌንስ እንዲህ አስቀምጦታል……..

በ2018 ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስተር በመሆን የተቋቋመው የእርቀሰላም ኮሚሽን ብቸኛ ተቃውሞ የገጠመው በህውሃት የፓርላማ አባላት ነበር ። ዲሴምበር 2019 ላይ ደግሞ የቀድሞ የኢህአደግ ግንባር ወደ አንድ ፓርቲ ለማምጣት በጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረበው ሐሳብ የቀድሞ የኢህአዴግ ግንባር መስራች ህውሃት ሃሳቡን ውድቅ በማድረግ ራሴን አላከስምም በማለት በመቃወም ራሱን አገለለ ።

ብዙም ሳይቆይ የምርጫ ስኬጁዋል ሲወጣ ባሳለፍነው አመት ለማድረግ ተወስኖ የነበረ ቢሆንም ጁን 2020 ላይ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስብሰባ በማድረግ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በመከሰቱ ምክንያት በሽታው ሊያዛምተው ይችላል በሚል በአብላጫ ድምፅ በጊዜ ሰሌዳው መሰረት ተይዞ የነበረው የምርጫ ግዜ እንዲራዘም ተወሰነ።

 ………….ህውሃት በበኩሉ ምርጫው ለኮቪድ የሚደረገው ጥንቃቄ ተወስዶ መደረግ አለበት የሚል ሐሳብ እንዳለው በመግለፅ ህውሃትም ስብሰባ አድርጎ በአብላጫ ድምፅ … ምርጫው ለብቻው ለማድረግ ወሰነ ። ሴፕቴምበር 5/2020 ደግሞ የፌደሬሽኑ ምክር ቤት ህውሃት የሚያደርገው ምርጫ ህጋዊ ያልሆነ አንድ የምርጫ ኮሚሽን ብቻ ስለሆነ ያለው ከሎሚሽኑ ውሳኔ ማፈንገጥ አይችልም በማለት ገለፀ ።

ህውሃትም ምርጫው ለማራዘም ተገቢ ምክንያት ስለሌለ ህገ መንግሥቱ ባስቀመጠው ወቅትና ሰዓት አደርጋለሁ የምርጫ ኮሚሽንም አቋቁማለሁ አለ ።

የፌደሬሽኑ ምክረ ቤትም ህውሃት ምርጫውን የሚያካሂድ ከሆነ መከላከያው ሕግ እንዲያስከብር እናደርጋለንም አለ። …..ሆኖም ህውሃት በፌደራል የመንግሥቱ ይሁንታ በጣሰ መልኩ የምርጫ ኮሚሽን አቋቋመ። …….ሴፕቴምበር 9/2020 ደግሞ የሕውሃት ምርጫ ያለ ምርጫ ቦርድ ፈቃድ ያለ ፌደሬሽን ምክር ቤት ፈቃድ ያለ ሕዝብ ተወካዮች ፈቃድ አደረገ። በምርጫውም ሙሉ ለሙሉ በሚባል መልኩ ሁሉንም መቀመጫዎች ጠቀለለ ።

ኦክቶበር 5/2020 ህውሃት ሁሉንም በፌደራል መንግሥት በኩል ያሉት ሁሉንም ተወካዮቹ ፓርላማውን ጥለው እንዲወጡ ትእዛዝ አስተላለፈ። …………..ከዚህ ከምርጫው መተላለፍ እና በሕገመንግሥቱ የተቀመጠው አወዛጋቢ የሕግ ክፍተት አስመልክቶ ህውሃት የፌደራል መንግሥቱ የሃገሪቱ ሎአላዊ መንግሥት አይደለምና ፓርላማው መበተን አለበት የሚል አቋምም ያዘ ።

 ኦክቶበር 7/20202 የፌደሬሽን ምክር ቤት በትግራይ ገዥ በሆነው ህውሃት ላይ በጀት እንዲቋረጥበት ወሰነ ። ከዚሁ ጋር ተያይዞ የገንዘብ ኖት ቅያሪም በተከታታይ ተከናወነ ።

ኦክቶበር 29/2020 ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ የሰሜን እዝ መሪ በመቀየር ወደ ቦታው ላኩ፤ ሆኖም የህውሃት ባለሥልጣናት አብይ አህመድ ኮማንደር ጀነራል የመቀየር ሕጋዊ ሰውነት የለውም በማለት ውድቅ አድርገው ወደ ሰሜን የተላከው ጀነራል ተመልሰ ።በህውሃት አመለካከት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጊዜው ኤክስፓየርድ አድረጓል እኛል ሊመራን አይችልም ጀነራልም መቀየር አይችልም ነው ባጭሩ። ……

ከዛ ኖቬንበር 4/20202 ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ በሰሜን እዙ ላይ በህውሃት ጥቃት መሰንዘሩን ገልፀው ሰራዊቱ የተቃጣበትን ዘመቻ ማምከን እንዳለበት በመግለፅ መከላከያ ሠራዊቱ ከህውሃት ጁንታ ግር መግጠም የመጨረሻ …..point of no return ላይ ደርሶ የእርስ በርስ ጦርነቱ አንዲጀመር ሆኗል ።

ታዲያ ይሄ የኹለቱ የቃላት ጦርነት ሂደት ካየን በኹለቱ መካከል ሰላም የማውረድ እርቅ የመፈፀም ነገሮች የማያግባቡ ከሆነ የሚያግባበው ጦርነት ነው ብለዋል። …..

እና በዚህ መልኩ ስናየው አንዳንዳንዶች እንደሚቦረተፉት ድንገት የተከሰተ አይደለም እነዚህ ሰዎች የሚያነሱት ሐሳብ ህውሃት መከላከያው ላይ ሰንዝሯል የሚል ነው። …..ቀለል ያለ ምሳሌ ልስጥ አርሜኒያና አዘርባጃኖች መጀመሪያ በድንበሩ ምክንያት ሲወዛገቡ ነበር በሰላም መፍታት አልቻሉም ስለዚህ ቀድሞ አንዱ ወደ አንደኛው ይተኩስና ጦርነቱ ይጀመራል ….ኹለቱም አካል በተመሳሳይ እንዲተኩሱ እንዲያጠቁ አይጠበቅም።

 …ስለዚህ ህውሃት ሰሜን እዝላይ ሰነዘረ ቢባል ከጦርነት ቴክኒክ አኳያ የሚያስጮህ አይደለም ደሞ መጠየቅ አስፈላጊ ነው። ህውሃት ለምን ጦርነቱ አፈጠነው ? ብሎ አናላይዝ ማድረግ ያስፈልጋል ጦርነቱ ህውሃት ጠቃሚ ስለሆነለት ነው። ምክንያቱም ህውሃት በጀት የለውም በፌደራል መንግሥቱም ማነቆ ውስጥ ነው በዚህ መልኩ እየቆየ ከመጣ ራሱ በራሱ ስዊሳይድ መፈፀሙ አይቀሬ መሆኑን የተረዳ ይመስላል ።

 የትግራየ ሕዝብ የሚበላው ካጣ መሪውን የማይበላበት ምክንያት አይኖርም ለዚህ ሲባል ብዙ ኢኮኖሚያዊ ጉዳት ሳይደርስባቸው መጀመር ለነሱ የሞት ሽረት ጉዳይ ነበርና ።ሌላው ህውሃት የአገሪቱ ሉአላዊነት ተዳፍሯል የሚበላው ነገር ነው መከላከያው አገር ብቻ ሳይሆን መንግሥትንም ጭምር ነው የሚጠብቀው።

 ስለዚህ ህውሃት አብይ ጋር ለመድረስ መከላከያውን መደምሰስ መተንኮስ አለበት ሎጂካል ሆነን ስናየው  ልክ እንደ ደርግ ማለት ነው የደርግ መንግሥት በህውሃት የወደቀው መጀመሪያ መከላከያው በቁጥጥር ስር ካዋለ በኋላ ነበር ስለዚህ በኹለት መልኩ ማየት ተገቢ ነው እላለሁ። ሳጠቃልለው ጦርነቱ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ቢሆን ኤክስትራ ዳሜጅ ሳናስከትል በቀላሉ መቋጨት ይቻላል። ሆኖም ጦርነቱ ከተመረጠ ግን ህውሃት ወደ ስልጣን ዳግም የሚንደረደርበት አጋጣሚ ስለሆነ ያ በአስከፊ አፋኝነቱ የምናውቀው አስቀያሚ ስርዓት ደግሞ ወደስልጣን  እንዲመጣ መፍቀድ ግን ተገቢ አይሆንም።

 ….በተጨማሪ ለጊዜውም ቢሆን ለአገር አንድነት ሲባል ከፌደራል መንግስቱ እና ከመከላከያ ሰራዊቱ ጎን መቆምም አስፈላጊ ነው …….. ምክንያቱም በኢትዮጵያ አንድ መንግሥት ብቻ መኖሩን መረጋገጥ አለበት ለዚህ ደግሞ ህውሃት መወገድ /መንበርከክ ይኖርበታል የሚለው የበለጠ ያሳምነኛል ። ስደመድመው ማኅበራዊ ሚዲያው መርዙን ከመርጨት ሰከን ብሎ ስለ ሰላም እርቅ ቢሆን ጥሩ ነውካልሆነ ግን የሌለ በሬ ወለደ ባይስተጋባበት ሚዛናዊ ቢሆን እላለሁ …………….

በጁሃር ሳዲቅ (ጋዜጠኛ)colomunistjuhar@gimal.com

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here