የመንግሥት የፋይናንስ ድርጅቶች በ2013 በጀት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ከታክስ በፊት ብር 3ነጥብ8 ቢሊዮን አተረፉ

0
823

በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ሥር በፋይናንስ ዘርፍ የሚገኙ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፣የኢትዮጵያ መድን ድርጅት እና የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በ2013 በጀት የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት በጊዚያዊ የሂሳብ መረጃ መሠረት ከታክስ በፊት በድምሩ 3.8 ቢሊዮን ማትረፋቸው ተነግሯል፡፡

ይህ አፈጻጸም የልማት ድርጅቶቹ አቅደውት ከነበረው የብር 4.36 ቢሊዮን ትርፍ አንጻር ሲታይ ክንውናቸው ከዕቅዳቸው 87.35 በመቶ እንደሆነ የድርጅቶቹ አፈጻጸም ህዳር 8፣14 እና 15 / 2013 . በተገመገመበት ወቅት ታውቋል፡፡

የግምገማ መድረኩን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር  ሀብታሙ ኃይለሚካኤል የመሩት ሲሆን፣የየልማት ድርጅቶቹ የቦርድ ተወካዮች፣ዋና ሥራ አስፈጻሚዎች፣የማኔጅመንት አባላትና እንዲሁም የኤጀንሲው የፋይናንስ ድርጅቶች ዘርፍ ዳይሬክተር እና ባለሙያዎች በግምገማው ተሳትፈዋል፡፡

ድርጅቶቹ ይህንን ትርፍ ሊያገኙ የቻሉት የባንክና የመድን አገልግሎቶች በመስጠት በሩብ ዓመቱ ብር 19.99 ቢሊዮን ገቢ ለማግኘት አቅደው ብር 18.89 ቢሊዮን ወይም የዕቅዳቸውን 95 በመቶ ማግኘት በመቻላቸው ነው ተብሏል፡፡

ከተገኘው ከአጠቃላዩ የብር 3.8 ቢሊዮን ትርፍ ከፍተኛውን ብር 3.1 ቢሊዮን ወይም ከዕቅዱ 78 በመቶ በማትረፍ የዘርፉ ትርፍ አፈጻጸም 81.23 በመቶ ያህል ድርሻ የያዘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲሆን፣በአምናው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት አፈጻጸሙን አሻሽሎ ከኪሳራ የወጣው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በአጠቃላይ በሩብ ዓመቱ ብር 455 ሚሊዮን ወይም የዕቅዱን 2351 በመቶ ሊያተርፍ መቻሉም ተገልጿል፡፡

በዚህም ለዘርፉ አጠቃላይ ትርፍ የ11.93 በመቶ አስተዋጽኦ በማድረግ ኹለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ደግሞ በሩብ ዓመቱ ብር 260.56 ሚሊዮን ወይም የዕቅዱን 75 በመቶ አትርፎ ለዘርፉ ትርፍ አፈጻጸም የ6.83 በመቶ ድርሻ በማበርከት ሶስተኛ ደረጃ ይዟል፡፡

በየግምገማዎቹ ማጠቃለያ ላይ የድርጅቶቹ የመጀመሪያ መንፈቅ ዓመት አፈጻጸም አበረታች በመሆኑ በቀጣዮቹ የ2013 በጀት ዓመት የትግበራ ምዕራፎች የየድርጅቶቹ ቦርዶች፣የማኔጅመንት አባላትና መላው ሠራተኛ ይህንኑ አጠናክረው እንዲቀጥሉና በበጀት ዓመቱ ከፍተኛ ውጤት እንዲያስመዘግቡ አቅጣጫ ተሰጥቶ ግምገማው ተጠናቋል፡፡

 

 

 

 

 

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here