“ውጪ ያሉ ዲፕሎማቶቻችንን እንቅልፍ እየነሳናቸው ነው” አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

0
951

አሁን አገራችን ያለችበትን ሁኔታ የተለየ በመሆኑ ኢትዮጵን በውጪ አገራት የወከሉ አምባሳደሮቻችንን እና የሚሲዮን መሪዎችን ተግተው እንዲሰሩ እንቅልፍ እየነሳናቸው ነው በማለት የውጪ ጉዳይ ሚኒንስተር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናገሩ።
አሁን አገራችን ያለችበት ሁኔታ የተለየ ነው፣በተለመደው መልኩ መቀጠል አይቻልም፣ሪሴብሽን ሄዶ ብርጭቆ አጋጭቶ መምጣት፣ስብሰባዎችን ተካፍሎ መምጣት አይቻልም ባጭሩ ‹ቢዝነስ አስ ዩዡዋል› መቀጠል አይቻል፣ ከዚያም ያለፈ ሥራ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል። አምባሳደር ዲና

በዚህም በየሳምንቱ የተሰሩ ሥራዎችን ከሪፖርት ባለፈ በምስል እና በድምጽ እንዲሁም በሌሎች ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ጭምር አስደግፈው የሰሩትን ተጨባጭ ሥራዎች አንደሚልኩ እና ክትትል አንደሚደረግ ተናግረዋል።
በውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለሚያደርጉት የተለያዩ እንቅስቃሴዎች ኢምባሲዎቻችን ድጋፍ አያደርጉላቸው አይደለም እየተባለ ለሚነሳው ወቀሳ ቃል አቀባዩ ሲመልሱ ሁለት ነገሮችን ማየት እንደሚያስፈልግ እና እንደዚህ አይነት አንቅስቃሴዎች ‹ኢንዲፔንደንት› እንቅስቃሴዎች መሆናቸው በራሱ ጥሩ እንደሆነ ተናግረዋል።

በራስ ተነሳሽነት የሚደረጉ መሆናቸው እንዳውም ተመራጭ ነው። ይህም ሆኖ ግን የኢትዮጵያ ኢምባሲዎች መረጃ በመስጠት ድጋፍ ማድረግ አለባቸው ብለዋል። አስፈላጊ ሲሆንም ማስተባባር ሊያስፈልግ ይገባል ብለዋል።
የኢትዮጵውያን ማህበረሰብ በራሳቸው ተነሳሽነት በህዳሴ ግድብ ላይ በትራፕ አስተዳደር የነበረውን ጣልቃ ገብነት እንዲሁም በወቅታዊው የትግራይ ጉዳይ የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታ ምክር ቤት በአየርላንድ አማካኝነት በኢትየጵያ በውስጥ ጉዳይ ላይ ጣልቃ ለመግባት የሚያደረገውን እንቅስቃሴ በመቃወም ያደረጉትን እንቅስቃሴ ናቸው።ከመንግስት እና ከፓርቲ ጋር የሚያያዙ ሆነው መቆጠር አይገባቸውም።

ባለፈው ሳምንት በሰሜን አሜሪካ ማለትም በአሜሪካ እና በካናዳ በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች እንዲሁም በአውሮፓ ጭምር ኢትዮጵያ ላይ የሚደረጉ ጣልቃ ገብነቶች አንዲቆሙ እና በሰብአዊ እርዳታ ሰበብ ጣልቃ እነዳይገቡ የሚያሳስብ ሰልፎች ማከናወናቸው ይታወሳል።
ትልቅ አገራዊ ጉዳይ ላይ የተከናወነ የድጋፍ ሰልፍ በመሆኑ እና ትልቅ ተጽእኖ የፈጠረ ጉዳይ መሆኑንም እያየናቸው ከመጣናቸው ምልክቶች አንረዳለን ብለዋል።ብለዋል አምባሳደር ዲና።

አሜሪካም በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ በሚደረገው ድርድር ሶስቱም አገራት ካልጋበዟት በስተቀር አገራቱን ለማደራደር ጣልቃ እንደማትገባ በውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የቀጠናዊ ጉዳዮች ቃል አቀባይ ሳሙኤል ዋርበርግነርም አማካኛነት ማስታወቋ ይታወሳል።
የአባይ ወንዝ ለግብጽ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያም ለሱዳንም በጣም ጠቃሚ ወንዝ መሆኑን አሜሪካ ታምናለች ብለዋል። በአገራቱ መካከል ያለው ልዩነት በውይይትና በድርድር እንዲፈታ አገራቸው ድጋፍ ማድረጋን እንደምትቀጥል ቃል አቀባዩ ገልጸዋል።

የሌሎች አገሮች ጩሀቶች እና ተጽእኖዎች በተመሳሳይ እየቀነሱ እንደመጡ አምባሳደሩ ተናግረዋል። ነገር ግን በዲፕሎማሲው መስክ ውጤቶች ቢገኙም ድክመቶች መኖራቸው የሚካድ አይደለም ብለዋል አምባሳር ዲና ኮንቬንሽናል የዲፕሎማሲው የስራ መስመር እንዳለ ሆኖ የሲቪል ማህበረሰቡ የኮምዩኒቲዎች ፣ተጽእኖ ፈጣሪዎችን ሳይቀር በማግኘት ሥራዎችን መስራት አስፈላጊ ነው ብለዋል። ተሳትፎ በዲጅታል ቴክኖሎጂ ጭምር የታገዘም መሆን እንዳለበት እና ለዚህም በዋናው መሥሪያ ቤት ደረጃ ሁልጊዜም ምክከር እያደርግን ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያ ውጪ ጉዳይ ሚንስትር ዋና መሥሪያ ቤት በተከናወኑ ሥራዎች ሳይረካ ወቅቱም የሚጠይቀውን ሥራ በመሥራት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።


ቅጽ 2 ቁጥር 124 መጋቢት 11 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here